በሞዛምቢክ ፖለቲካዊ ቀውስ ሳቢያ ከ1500 እስረኞች ከሞዛምቢክ እስርቤት አምልጠዋል። ሰላሳሶስት ሰዎች ወዲያው የተገደሉ መሆናቸው እና 15 ሰዎች ከጠባቂዎች ጋር ግጭት በመፈጠሩ መጎዳታቸው ተነግሯል። ፖሊስ 150 ያመለጡ እስረኞችን መያዙን አስታውቋል። የሞዛምቢክ ከፍተኛ ፍርድ ቤት ሰኞ እለት ፍላሚንጎ ፓርቲ ምርጫውን ማሸነፉን ይፋ ማድረጉን ተከትሎ በሀገሪቱ ሁከት መነሳቱ ቢቢሲ ዘግቧል። በ-እስክንድር ከበደ