፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ታህሳስ 21 2017| NBC ETHIOPIA- በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና አካባቢው የሽብር ወንጀል በፈፀሙ 81 አሸባሪዎች ላይ ከ 20 ዓመት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እሥራት የፍርድ ውሳኔ እንደተላለፈባቸው የፌዴራል ፖሊስ አስታውቋል።
በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና አካባቢው የሽብር ወንጀል በፈፀሙ 27 አሸባሪዎች ላይ ከ23 ዓመት እስከ 1 ዓመት ከ6 ወር የሚደርስ ፅኑ እስራት እንደተፈረደባቸው ታህሳስ 11 ቀን 2017 ዓ.ም የፌዴራል ፖሊስ መግለፁ ይታወሳል።
በተጨማሪ በኦሮሚያ ክልል ምዕራብ ሀረርጌ ዞን እና አካባቢው የሕዝቡን ሰላምና ደህንነት በማደፍረስ፣ ንፁሃን በመግደል፣ በጦር መሣሪያ የታገዘ ዝርፊያ እና የእገታ ወንጀል ሲፈጸሙ በፀጥታ ኃይሎች በተካሄደው ኦፕሬሽን በቁጥጥር ሥር ውለው የኢትዮጵያ ፌዴራል ፖሊስ ድርጊቱን በሰው እና በሰነድ ማስረጃ በሚገባ አጣርቶ አቃቢ ሕግ ክስ መመስረቱን የፌዴራል ፖሊስ መረጃ ያሳያል።
ጉዳዩን የተመለከተው የፌደራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ድሬዳዋ ምድብ ታህሳስ 18 ቀን 2017 ዓ.ም በዋለው ችሎት ተከሳሾቹን ያስተምራል ሌሎችንም ያስጠነቅቃል በማለት ፎቶግራፋቸው ከዚህ በታች በተመለከተው አሸባሪዎች ላይ ከ20 ዓመት እስከ 10 ዓመት ፅኑ እስራት የሚደርስ ውሳኔ አስተላልፎባቸዋል።












