፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 18 2017| NBC ETHIOPIA -በደቡብ ኮርያ የተሰራው ባለአራት እግር ሮቦት ላይቦ 2 (Laibo 2) በአንድ ቻርጅ ሙሉ ማራቶን ሮጦ በማጠናቀቅ የመጀመሪያ ሮቦት ሆኗል።
በKAIST (Korea Advanced Institute of Science and Technology) የተሰራው ይህ ሮቦት 42 ኪ.ግ. የሚመዝን ሲሆን ማራቶኑን ሮጦ ያጠናቀቀው በ4:19:52 ሲሆን በሩጫው ወቅት ዳገታማና ቁልቁለታማ ቦታዎችን ማለፍ፣ ከሌሎች ሯጮች ጋር ላለመጋጨት ተገቢውን ርቀት መጠበቅና የባትሪ አጠቃቀሙን እንደአስፈላጊነቱ በመቀያየር የመጨረሻው መስመር ላይ መድረሱን ማረጋገጥ ነበረበት።

ይህ አዲስ ሮቦት ከበፊት ስሪቶቹ የበለጠ የባትሪ አቅም ብቻ ሳይሆን ባትሪውን በተሻለ መንገድ መጠቀም የሚያስችለው የሰውሰራሽ አስተውሎት ጭምር የተገጠመለት ነው።
በተጨማሪም በፊቱና በጀርባው ላይ የተገጠሙ ሁለት ካሜራዎችን በመጠቀም በዙሪያው ያለውን የመሬት አቀማመጥ መረዳት የሚችል ሲሆን በእግሮቹ መገጣጠሚያዎች ላይ የሚገኙ ዳሳሽ ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም የሀይል ፍጆታውን እንደአስፈላጊነቱ መጨመርና መቀነስ የሚችል ነው።
የሮቦቱን በተራራማ አካባቢዎችና በአደጋ ቀጠናዎች የመንቀሳቀስ ችሎታ ለማሻሻል እየሰሩ መሆኑን የሮቦቱ ባለቤት ተናግረዋል። ዘገባው የኦዲቲ ሴንትራል ነው።
በ-ዳንኤል መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












