፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ህዳር 17 2017| NBC ETHIOPIA -የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ከሱዳን የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር አሊ ዩሴፍ አህመድ አልሸሪፍን ዛሬ ጠዋት በቢሮቸው ተቀብለው ተወያይተዋል ።
ሁለቱ ሚኒስትሮች በሁለትዮሽ ጉዳዮችና በሱዳን ወቅታዊ ሁኔታ ላይ ተወያይተዋል፡፡
የሱዳኑ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በሱዳን ያሉ ልማቶችን በተመለከተ ገለጻ ያደረጉ ሲሆን ግጭቱን ሸሽተው የነበሩ የሱዳን ዜጎችን በመቀበል ኢትዮጵያ ላደረገችው ደማቅ መስተንግዶና ድጋፍ በሱዳን ህዝብ ስም ምስጋና አቅርበዋል፡፡

ዶ/ር ጌዲዮን ኢትዮጵያ ለሱዳን ያላትን አጋርነት አረጋግጠዋል ፤ የሱዳን ወንድሞቻችንን ማስተናገድ የጎረቤት ግዴታችን ነው ብለዋል፡፡ የሱዳን ግጭት የሀገሪቱን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነት ባከበረ መልኩ ሰላማዊ በሆነ መንገድ እንዲፈታ ፍላጎት እንዳላት እና ኢትዮጵያ ድጋፏን እንደምትቀጥል ገልፀዋል።
በታላቁ የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብ (GERD) ድርድርን ጨምሮ በሌሎች ጉዳዮች ላይ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ጌድዮን ጢሞቴዎስ ቀጥተኛ ንግግር እንደሚያስፈልግ አብራርተዋል፡፡
ሚኒስትሮቹ መደበኛ የሁለትዮሽ ፖለቲካዊ ትስስር ለማጠናከር፣ ሰላምና መረጋጋትን ለማስፈን ስምምነት ላይ መድረሳቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook- https://web.facebook.com/ethiopiannbc/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBCEthiopia
#ሆኖ_መገኘት












