፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
የሩሲያው ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን ለዶናልድ ትራምፕ የእንኳን ተመረጡ መልዕክት አስተላለፉ፡፡
ፑቲን በትራምፕ መመረጥ ዙሪያ ዝምታን መርጠው ሰዓታት አልፈው ነበር ፡፡
የቭላድሚር ፑቲን መልዕክት የተሰማው በሶቺ ጥቁር ባህር ሪዞርት በአንድ ዓለም አቀፋ ፎረም ላይ ንግግር ማድረጋቸውን ተከትሎ ነው፡፡
የዩክሬንን ጦርነት በተመለከተ መፍትሄ ለመስጠትና የሩሲያንና የአሜሪካን ግንኙት በተመለከተ ትራምፕ ያነሱትን ሀሳብ ፑቲን ሰምተውታል ተብሏል፡፡
ፑቲን የሚሆነውን ሁሉ እናያለን ፤ለአሁኑ የምለው ነገር የለም ብለዋል፡፡
ክሬሚሊን ትራምፕ የዩክሬኑን ጦርት ስለመቋጨት ያላቸውን ውጥን በበጎ እንደሚመለከተው ከዚህ ቀደም መግለጹ ይታወሳል ዘገባው የሞስኮ ታይምስና የኤቢሲ ኒውስ ነው፡፡
በ-ቢኒያም ካሴ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook-https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












