፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 29 2017| NBC ETHIOPIA-ከሰላሳ በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ250 በላይ ድርጅቶች የተሳተፉበት 10ኛው የአፍሪካ ሶርሲንግና የፋሽን ኤግዚቪሽን ሳምንት በአዲስ አበባ ተከፍቷል።
በመክፈቻ ስነ-ስርዓቱ የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል፣ የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳና ዲፕሎማቶች ተገኝተዋል።
ኤግዚቢሽኑ ከዛሬ ጀምሮ ለአራት ተከታታይ ቀናት የሚካሄድ ሲሆን ከሰላሳ በላይ ሀገራት የተውጣጡ ከ250 በላይ በጨርቃ ጨርቅ፣ በቆዳና በፋሽን ዘርፍ የተሰማሩ አምራቾች ምርትና አገልግሎታቸውን ያስተዋውቁበታል እንዲሁም ከ60 በላይ ሀገራት የተውጣጡ 7 ሺህ ነጋዴዎች ይሳተፉበታል።

ኤግዚቢሽኑ በዘርፉ የተሰማሩ ኢትዮጵያውያን አለም በጨርቃ ጨርቅና በቆዳ ኢንዱስትሪ የደረሰችበትን ደረጃ እንዲረዱ እድል የሚፈጥርላቸው መሆኑ ሲገለጽ መድረኩ በዘርፉ የተሰማሩ አምራቾች ከአቻ ተቋማት ጋር ምርታቸውን ማስተዋወቅ የሚያስችሉ ውይይቶችና የልምድ ልውውጥ እንዲያደርጉ እንዲሁም የገበያ ትስስር እንዲፈጥሩ እንደሚረዳቸው የኢንዱስትሪ ሚኒስትር መላኩ አለበል ተናግረዋል፡፡
ሚኒስትሩ አክለውም ኢትዮጵያ በአምራች ኢንዱስትሪው ዘርፍ የሀገር ውስጥና የውጭ ባለሀብቶች ኢንቨስት እንዲያደርጉ ምቹ ሁኔታ መፍጠሯንም አስታውቀዋል በዚህም ኢንዱስትሪ ፓርኮችን በማስፋፋትና መሰረተ ልማት በማሟላት በስፋት መሰራቱን ነው ያስረዱት።
የቱሪዝም ሚኒስትር ሰላማዊት ካሳ በበኩላቸው ኢትዮጵያ የጨርቃ ጨርቅና የቆዳ ምርቶችን የመጠቀም የረጅም አመት ልምድና ታሪክ እንዳላት ተናግረው ኤግዚቢሽኑ የቱሪዝምና የንግድ እንቅስቃሴን ለማነቃቃት ትልቅ ፋይዳ እንዳለው ጠቁመዋል ዘገባው የኢዜአ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Facebook – https://www.facebook.com/












