፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 29 2017| NBC ETHIOPIA-በጎንደር ከተማ ጉብኝት እያደረጉ የሚገኙት የአማራ ክልል ርዕሰ መስተዳድር አቶ አረጋ ከበደ በፌደራል መንግሥት እየተከናወኑ ያሉ የልማት ፕሮጀክቶችን ጎብኝተዋል።
ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ የመገጭ ግድብ ፣ የአፄ ፋሲል አብያተ መንግሥት የቅርስ ጥገና ፣ የኮሪደር ልማት ስራ እና የጎንደር አዘዞ የአስፓልት ኮንክሪት መንገድ ግንባታን የስራ እንቅስቃሴ ተመልክተዋል።
ርዕሰ መስተዳድሩ በዚህ ጉብኘታቸው ወቅት በጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) አመራር ሰጭነት እየተከናወኑ የሚገኙ የፌደራል መንግስት ፕሮጀክቶች በጥሩ የአፈጻጸም ደረጃ ላይ እንደሚገኙ ገልጸዋል መረጃው የክልሉ ኮሙኒኬሽን ቢሮ ነው።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












