፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 22 2017| NBC ETHIOPIA-የግብርና ሚኒሰቴር ባለፉት 100 ቀናት የተሰሩ ስራዎችን አስመልክቶ ለመገናኛ ብዙሃን መግለጫ ሰጥቷል።
በመኸር የእርሻ ወቅት 22.3 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል የተሸፈነ ሲሆን 20.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በአነስተኛ አርሶአደሮች በሰብል መሸፈኑን ተገልጿል በሰብል ከተሸፈነው መሬትም በቆላማ አአካባቢዎች መሰብሰብ መጀመሩ ሚኒስትሩ ገልፀው 1 .7 ሚሊየን ኩምታል ምርት ተሰብስቧል ብለዋል።
ሚኒስትሩ በመግለጫቸው 2016 የበልግ እርሻ ወቅት 83 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰቡን አብራርተዋል ። እንዲሁም በበልግ እርሻ 3.4 ሚሊዮን ሄክታር መሬት በሰብል ተሸፍኖ የነበር ሲሆን ምርቱም ሙሉ ለሙሉ ተሰብስቦ ማለቁ የግብርና ሚኒስትሩ ገልጸዋል ።በዚህም 83 ሚሊዮን ኩንታል ምርት መሰብሰብ መቻሉን አንስተዋል።
ለዘንድሮው የበጋ መስኖ ዝግጅት መጀመሩ የተገለፀ ሲሆን 4.2 ሚሊዮን ሄክታር በስንዴ ለመሸፈን መታቀዱ ተጠቁሟል በዚህም 173 ሚሊዮን ኩንታል ስንዴ ለማግኘት ታቅዷል።
በተያዘው በጀት አመት በክረምት እና በበጋ 8.2ሚሊዮን ሄክታር መሬት በስንዴ በመሸፈን 300 ሚሊየን ኩምታል ምርት ለማግኘት መተቀዱን የግብር ሚኒስትር ገልጸዋል ።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












