፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 23 2017| NBC ETHIOPIA-የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ የአለም የቱሪዝም ቀን አስመልክቶ የሲምፖዚየም ውይይት ማስፈፀሚያ እያካሄደ ነው ።
“ቱሪዝም ለሰላም” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ የሚገኘው የአለም የቱሪዝም ቀን ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝም ሀብት በማስተዋወቅ እየተከበረ መሆኑን የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር ባህል ኪነ-ጥበብና ቱሪዝም ቢሮ ኃላፊ ሂሩት ካሳው(ዶ/ር) ተናግረዋል።
ቱሪዝም እና ሰላም ያላቸው ግንኙነት ጥብቅ በመሆኑ ቱሪዝምን በመጠቀም ሰላምን ማምጣት እንችላለን ነው ያሉት።
የኢትዮጵያ ቱሪዝም መሰረቱን ያደረገው በባህል ላይ መሆኑ እና ባህል ለችግሮች መፍቻ ቁልፍ እንደሆነ ተመላክቷል። በመድረኩ ሰላምና ቱሪዝምን አስመልክቶ ጥናታዊ ጽሁፍ ቀርቧል።
በ-የአብስራ ብርሃኑ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Facebook – https://www.facebook.com/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












