፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጥቅምት 22 2017| NBC ETHIOPIA-አምባሳደሮችና ዲፕሎማቶች ወቅታዊውን የዓለም ጂኦ-ፖለቲካ አካሄድ ከግንዛቤ ውስጥ በማስገባት የኢትዮጵያን ብሔራዊ ጥቅም በተሻለ ሁኔታ ለማስጠበቅ ትኩረት ሰጥተው መስራት አለባቸው ሲሉ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ጌዲዮን ጢሞቴዎስ(ዶ/ር) ገለጹ።
ሚኒስትሩ ይሄንን ያሉት በመላው ዓለም ከሚገኙ የኢትዮጵያ ኤምባሲዎች እና ቆንስላ ጄኔራል ጽሕፈት ቤቶች ኃላፊዎች ጋር በበይነ መረብ ባደረጉት ውይይት ላይ ነው።
በዚሁ ወቅትም የኢትዮጵያን የሁለትዮሽ እና የባለብዙ ወገን የዲፕሎማሲ ግንኙነቶች የበለጠ ለማጠናከር በጠንካራ ቅንጅታዊ አሠራር መንቀሳቀስ እንደሚገባ ሚኒስትሩ ማሳሰባቸውን ከውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የተገኘው መረጃ ያመለክታል።












