፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 30 2017| NBC ETHIOPIA- የአሜሪካዋ ፍሎሪዳ ግዛት ምዕራባዊ የባህር ዳርቻ አስፈሪ በተባለለት ሀሪኬን ሚልተን በተባለ ከባድ ማዕበል መመታቷ ተነግሯል።
ሀሪኬን ሚልተን ማዕበል ነፋስና ነጎድጓዳማ ዝናብ ያዘለ በመሆኑ ጉዳቱን ከባድ እንዳደረገው ነው የተገለጸው።



በግዛቲቱ የሚገኙ 3 ሚሊዮን መኖርያ እና ንግድ ቤቶችም በዚሁ ምክንያት የኤሌክትሪክ ሀይል እንዲቋረጥባቸው ሆኗል።
የአሜሪካ የአደጋ ጊዜ አገልግሎት ማዕበሉ በቀጣይ ቀናትም ከባድ ዝናብ፣ ጎርፍ እና አውዳሚ ነፋስ ሊያስከትል እንደሚችል አስጠንቅቋል።












