Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

የዛሬውን በውል የምንገነዘብ እና የምንተገብር መሪዎች ነን- ይርጋ ሲሳይ

October 9, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | መስከረም 28 2017| NBC ETHIOPIA-“የሕልም ጉልበት፣ ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ የስልጠና መርሐ ግብር በባሕር ዳር ተጀምሯል፡፡

በመርሐ ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ክልል ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ ስልጠናው ከክልል እስከ ወረዳ ድረስ ለተመረጡ መሪዎች የሚሰጥ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

የስልጠናው ዓላማ የአመለካከት እና የተግባር አንድነትን በማጎልበት፣ የመሪዎችን ሁለንተናዊ አቅም በመገንባት የብልጽግና ጉዞን ለማረጋገጥ መኾኑን ገልጸዋል፡፡ ሥልጠናው ዓላማ ጠንካራ ተቋማትን በመገንባት፣ ቅቡልነት ያለው ሀገረ መግንሥት የመገንባት እና ሀገራዊ ሕልምን ለማሳካት እንደሆነም ተናግረዋል፡፡

ብልጽግና ፓርቲ ትልቅ እና ግልጽ ሃሳብ ያለው ፓርቲ ነው ያሉት ኀላፊው የመሐል ፖለቲካን እንደሚከተልም አመላክተዋል፡፡ መነሻችን መደመር መዳረሻችን ደግሞ ብልጽግና ነው ብለዋል፡፡ በ2016 ዓ.ም የተሰጠውን ስልጠና በማጠናከር በድጋሜ በዚህ በጀት ዓመት ለመዋቅሩ በተደራጀ እና በተለየ ሁኔታ ስልጠና እየተሠጠ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዚህ ዓመት የሚሰጠው የመሪዎች ስልጠና በዓይነቱ የተለየ፣ ብዙ ሃሳቦችን የያዘ፣ ኢትዮጵያን በአፍሪካ ትልቅ ተምሳሌት የሚያደርግ፣ ተጽዕኖ የሚፈጥር ሀገር ለመገንባት የሚያስችል፣ ዜጎቿ የሚከበሩባት፣ ሰላም እና መረጋጋት የሚፈጠርባት፣ በልማት እና በመልካም አሥተዳደር የገጠመንን ስብራት የምንጠግንበት ትልቅ ስልጠና ነው ብለዋል፡፡

ፓርቲው ታላቅ ሕልም እንዳለውም ተናግረዋል፡፡ የትናንቱን መልካም እና በጎ ነገር የሚያስቀጥልና አቅም ያለው ፓርቲ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ የዛሬውን በውል የምንገነዘብ እና የምንተገብር መሪዎች ነን ብለዋል አቶ ይርጋ በመልእክታቸው፡፡ የነገውን የምንመለከትበት መነጸር እና ረጅም ሕልም ያለን መሪዎችን ነን ነው ያሉት፡፡

ብልጽግና ሪፎርሙ መሬት እንዲነካ በመሥራት ላይ እንደሚገኝም አስታውቀዋል፡፡ ሪፎርሙ ያጣነውን ዴሞክራሲ ለመትከል፣ የገጠሙንን የፖለቲካ ስብራቶች ለመጠገን፣ የሰው ልጆችን ተደማሪ ፍላጎት ለማሟላት፣ ማኅበራዊ እና ፖለቲካዊ ፍላጎትን ለማረጋገጥ የምንሄድበት ነው ብለዋል፡፡

የውስጣችንን ልዩነት በማጥበብ እና ኅብረ ብሔራዊ አንድነትን ለመገንባት የተጀመረውን የሕግ የበላይነት የማረጋገጥ ተልዕኮ ቅድሚያ ሰጥተን እንሠራለን ብለዋል፡፡ ሁሉም ተግባራት በተቋማት እና በተቀመጠው የሥራ ክፍፍል እንደሚፈጸም ነው የተናገሩት፡፡

ሁሉንም ተግባራት አቀናጅተን ስንመራ ክልሉ የገጠመውን ችግር በአጭር ጊዜ ቀርፈን፣ የሕዝባችንን ሁለንተናዊ ጥቅም እና የፓርቲውን ተልዕኮ እንፈጽማለን ነው ያሉት፡፡

መሪዎች በሥነ ምግባር እና በሞራል ተምሳሌት ልንሆን ይገባናልም ብለዋል፡፡ ለዚህ ደግሞ ማንም የሌለው እምቅ ባሕል፣ ወግ፣ እሴት፣ በአያቶቻችን የተሠሩ ታላላቅ ታሪኮች አሉን ያሉት አቶ ይርጋ እነዚህን እንደመስፈንጠሪያ በመጠቀም ለቀጣይ ትውልድ በማሸጋገር አሁናዊ የብልጽግና ጉዞን ማረጋገጥ ይገባል ነው ያሉት፡፡

ታላቅ፣ ግዙፍ፣ ተጽዕኖ ፈጣሪ እና የአፍሪካ ተምሳሌት የሆነች ሀገር መፍጠር ግድ ይለናልም ብለዋል፡፡ ስልጣናው የተሳካ እንዲኾን ሰልጣኞች ትኩረት እንዲያደርጉም አሳስበዋል፡፡

ለሰልጣኞች የገጠምንን የፖለቲካ እና የሰላም ስብራት የሚጠግን እና አቅም በሚፈጥር መልኩ ስልጠናውን እንድትከታተሉም አሳስባለሁ ነው ያሉት። የስልጠናው ግብ ጠንካራ ፓርቲ መፍጠር፣ የተጀመረውን ሪፎርም መሬት ማስነካት፣ የፓርቲውን እሳቤ እና ፍላጎት መረዳት እና መገንዘብ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ የሕዝብን እርካታ የሚያረጋግጡ ተቋማትን መፍጠር የሁልጊዜ ሥራ እንደሚኾንም ተናግረዋል፡፡ ሰላምን ማረጋገጥ፣ ፍትሕን ማስፈን የሚችሉ ተቋማትን መፍጠር የግድ ይላል ያሉት ኃላፊው ተቋማቱ አቅም ፈጥረው እና ጠንካራ ኾነው ሲቀጥሉ ጠንካራ መንግሥት መፍጠር ይቻላል ብለዋል፡፡

አባቶቻችን እና አያቶቻችን ባስረከቡን ሀገር ሃሳብን በመጠቀም በጥንካሬ በመሥራት ለውጭ እና ለውስጥ የማይበገር አቅም መፍጠር ይቻላል ነው ያሉት በመልእክታቸው ዘገባው የአሚኮ ነው፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

መሪን ሳንገነባ ሀገር ልንገነባ አንችልም-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

Next Post

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተሰበሰበ ካለው የሰሊጥ ሰብል ከ602 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተሰበሰበ ካለው የሰሊጥ ሰብል ከ602 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተሰበሰበ ካለው የሰሊጥ ሰብል ከ602 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልኩ ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለፀ

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልኩ ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለፀ

ቲክቶክ የህጻናትን አእምሮ ጤና በመጉዳት ተከሰሰ

ቲክቶክ የህጻናትን አእምሮ ጤና በመጉዳት ተከሰሰ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?