፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 29 2017| NBC ETHIOPIA- የብሔራዊ መታወቂያ ፕሮግራም ከአዲስ አበባ ሲቪል ምዝገባና የነዋሪነት አገልግሎት ጋር በመተባበር ከነገ መስከረም 30/2017 ጀምሮ የፋይዳ ዳጂታል መታወቂያን በዘመቻ መልኩ እንደሚሰጥ ተገልጿል።
የፋይዳ መታወቂያ ምዝገባ በዘመቻ መልኩ የሚሰጠው በአዲስ አበባ ከተማ መሆኑ የተገለፀ ሲሆን በሁሉም ወረዳዎች አገልግሎቱን ከሰኞ እስከ ቅዳሜ ማግኘት እንደሚቻል ተጠቁሟል።
በጋዜጣዊ መግለጫው ላይ በኢትዮጵያ ሀሰተኛ ሰነድ ከፍተኛ ስጋት እየሆነ መምጣቱም ተመላክቷል።
በአንድ ወር ውስጥ አዲስ አበባን ጨምሮ በመላው ኢትዮጵያ አንድ ሚሊየን ዜጎችን ለመመዝገብ እቅድ ተይዟል ተብሏል።
በ-አክረም ኑርያ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












