የእስራኤል መንግስት በኢራን ላይ የማያዳግምና የማያንሰራራ የበቀል እርማጃ ለመውሰድ ከአሜሪካ መንግስት ጋር መምከሩ ሲገለጽ የእስራኤሉ የመከላከያ ሚንስትር ዮአቭ ጋላንት በሰጡት ማብራሪያ ሀገራቸው በአራን ላይ የምትፈፅመው የበቀል ጥቃት ለድፍን ዓለም የሚያስደንቅ ነው ብለዋል ፤ ጋላንት አክለውም የኢራን ባለስልጣናት ምን እንደሚከሰት ፤ መቼ ምን እንደሚገጥቸው ስያወቁ ውጤቱን ያዩታል ነው ያሉት፡፡
ትናንት ረብዕ አመሻሽ ላይ የእስራኤሉ ጠ/ሚ/ር ቤንያሚን ኔታንያሁ ከአሜሪካው ፕሬዝዳንት ጆ ባይደን ጋር ሀገራቸው በኢራን ላይ ስለምትወስደው የበቀል ጥቃት ለሰላሳ ደቂቃ መምከራቸውን የሂንዱስታን ታይምስ ዘገባ ያስረዳል፡፡












