Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

መሪን ሳንገነባ ሀገር ልንገነባ አንችልም-ርዕሰ መስተዳድር አረጋ ከበደ

October 9, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨

አዲስ አበባ | መስከረም 28 2017| NBC ETHIOPIA-“የሕልም ጉልበት፣ ለእምርታዊ እድገት” በሚል መሪ ሃሳብ የሚሰጠው የብልጽግና ፓርቲ የስልጠና መርሐ ግብር በባሕር ዳር ተጀምሯል፡፡

በምርሐ ግብሩ ርዕሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ፣ በብልጽግና ፓርቲ የአማራ ብልጽግና ፓርቲ ቅርንጫፍ ጽሕፈት ቤት ኀላፊ ይርጋ ሲሳይ፣ ምክትል ርእሰ መስተዳድር አብዱ ሁሴን (ዶ.ር)፣ የክልሉ ከፍተኛ የመንግሥት እና የፓርቲ የሥራ ኀላፊዎች ተገኝተዋል፡፡

በመርሐ ግብሩ መልእክት ያስተላለፉት ርእሰ መሥተዳድር አረጋ ከበደ ብልጽግና ፓርቲ የሀገርን የረጅም ጊዜ ሕልም የኾነውን ሁለንተናዊ ብልጽግና የማረጋገጥ ትልም ለማሳካት እየሠራ መኾኑን ተናግረዋል፡፡ የመካከለኛ እና የረጅም ጊዜ ራዕይ እና ተልእኮ ቀርጾ እየተንቀሳቀሰ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡

ኢትዮጵያ በረጅም ጊዜ በምሥራቅ አፍሪካ፣ በአፍሪካ እና በዓለም ደረጃ ሊኖራት የሚችልበትን ደረጃ ታሳቢ ያደረገ ሥራ እየሠራ መሆኑንም አመላክተዋል፡፡ የነበሩ ችግሮችን በመሻገር የሚኖራትን የፖለቲካ፣ የምጣኔ ሃብት፣ የማኅበራዊ፣ የሰላም እና የዲፕሎማሲ ግቦች እና መዳረሻዎችን እንጥራና ግልጽ ግብ አስቀምጣ እየተንቀሳቀሰች መኾኗንም ገልጸዋል፡፡

ጠንካራ የፖለቲካ መረጋጋት፣ ሰላም የሰፈነባት፣ በዲፕሎማሲ በዓለም ተደማጭ የኾነች ሀገር ለመገንባት እየተሠራ መኾኑንም ተናግረዋል፡፡ ከዚህ ቀደም የተከማቹ ማነቆዎችን እና እዳዎችን አላቀን በመሻገር መዳረሻችን ላይ ግልጽ ግብ በማስቀመጥ እየሠራን ነው ብለዋል፡፡

ግቦችን ለማሳካት በመጀመሪያ ደረጃ ተቋም መገንባት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ በተቋም እና በፓርቲ ግንባታ ላይ በመመሥረት የምንፈልጋትን ሀገር ለዜጎቿ የተመቸች እንድትሆን አድርጎ ለመገንባት በግልጽ አስቀምጠናል ነው ያሉት፡፡

ተቋም እንገባ ስንል መሪ፣ ሠራተኛ እና ተገልጋይ እንገባ ማለት ነው ብለዋል፡፡ ሀገር እንገባ ሲባል የማኀበረሰብን ምጣኔ ሃብታዊ እና ማኅበራዊ ተጠቃሚነት ማረጋገጥ አለብን ነው ያሉት፡፡ የተቋም፣ የፓርቲና የሀገር ግንባታን ለማረጋገጥ ቀዳሚው መሪዎችን መገንባት መሆኑንም አንስተዋል፡፡

መሪን ሳንገነባ ሠራተኛን ልንገነባ አንችልም፣ መሪን ሳንገነባ ተገልጋይ ልናረካ አንችልም፣ መሪን ሳንገነባ ፓርቲ ልንገነባ አንችልም፣ መሪን ሳንገነባ ሀገር ልንገነባ አንችልም፣ መሪን ሳንገነባ መንግሥት ልንገነባ አንችልም ነው ያሉት፡፡ ዋናው ማዕከል መሪን መገንባት መኾኑንም አመላክተዋል፡፡

በተለይም የፖለቲካ መሪነት የፖለቲካ አውዱ ከሚፈጥራቸው ብዥታዎች በየጊዜው ማላቀቅ፣ ግልጽነትን የፈጠረ፣ ራዕዩን የተገነዘበ፣ ለሕልሙ የሚተጋ መሪን መፍጠር ይጠይቃል ነው ያሉት፡፡ ፓርቲው ለመሪነት ግንባታ ልዩ ትኩረት ሰጥቶ ሲንቀሳቀስ መቆየቱንም ተናግረዋል፡፡

ፓርቲው በተግባር ላይ የተመሠረተ እና የንድፈ ሃሳብ ስልጠናዎችን በማደራጀት የመሪዎች አቅም ግንባታ ሲፈጠር መቆየቱንም አስታውሰዋል፡፡ ፓርቲው የተጠኑ እና የተዳራጁ የተለያዩ ሥልጠናዎችን መስጠቱንም ገልጸዋል፡፡ የተሰጡ ስልጠናዎች መሪዎች የተቀራረበ አመላከከት እንዲኖራቸው ማድረጋቸውንም ተናግረዋል፡፡ ማኅበራዊ እና ተፈጥሯዊ ማንነቶች እንደተጠበቁ ኾኖ የፓርቲው መሪዎች አንድ የሚያደርጋቸውን አስኳል ጉዳይ ለይተው እንዲንቀሳቀሱ አስችሏል ነው ያሉት፡፡

አሁን የተጀመረው ስልጠናም ተጨማሪ አቅም የሚፈጥር መኾኑን ነው የተናገሩት፡፡ ሕልም ወይም ራዕይ መዳረሻን አውቆ ራስን ለማዘጋጀት ትልቅ መሳሪያ መኾኑንም ገልጸዋል፡፡ ዓላማ እና ራዕይ ሳይኖረው የሚንቀሳቀስ መሪ ውጤቱ ባለበት መርገጥ መኾኑንም አንስተዋል፡፡ ራዕያችን አስቀምጠን፣ በአቅጣጫችን ላይ ግልጽ ኾነን መንቀሳቀስ ይገባናል ብለዋል፡፡ ስልጠናው ድክመቶቻችን እና ጥንካሬዎቻችን በመለየት የሕልማችን ተጋሪዎች እንድንኾን እና ሕልማችንን እውን የሚያደርጉ ኃይሎችን እንድናሰባስብ፣ በራሱ የነቃ እና የተደራጀ አመራር እና ማኅበረሰብ እንድንፈጥርን የሚያደርግ ነው ብለዋል፡፡

ሕልማችን ለማሳካት ዓይነታዊ ለውጥ በማምጣት መንቀሳቀስ አለብን ነው ያሉት፡፡ ብዙ ፈተናዎች አሉብን ያሉት ርእሰ መሥተዳድሩ ከግራ እና ከቀኝ ያሉ ጽንፈኛ አመለካከቶች መኖራቸውንም ተናግረዋል፡፡ በፍጥነት መሻገር ግድ የሚሉ ችግሮች መኖራቸውንም ገልጸዋል፡፡ ችግሮችን አውቆ በፍጥነት መውጣት ይገባልም ብለዋል፡፡ አሁናዊ ሁኔታውን መገንዘብ እንደሚገባም አመላክተዋል፡፡ ሁለንተናዊ ውጤታመነትን ማረጋገጥ እንደሚገባም አስገንዝበዋል፡፡

በሁሉም መስክ ውጤታማነትን የሚያሻሽል ሥራ መስራት እንደሚጠበቅም ገልጸዋል፡፡ በማኅበረሰብ ቅቡልነት ያለው ሥነ ምግባር አዳብሮ መውጣት እንደሚገባም ተናግረዋል፡፡ የተሟላ ሥነ ምግባር ያለው መሪ መገንባት እንደሚያስፈልግም ገልጸዋል፡፡

ስልጠናው ስኬታማ እንዲኾን አሰልጣኞች እና ሰልጣኞች ትኩረት እንዲያደርጉም አስገንዝበዋል፡፡ በስልጠናው ሰፊ ውይይት የሚደረግበት እና ግልጽ አቋም የሚያዝበት መኾን አለበትም ብለዋል ዘገባው የአሚኮ ነው፡፡

ShareTweetShare
Previous Post

የሰሜን ኮሪያ በቆሻሻ የተሞሉ ባሉኖችን

Next Post

የዛሬውን በውል የምንገነዘብ እና የምንተገብር መሪዎች ነን- ይርጋ ሲሳይ

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
የዛሬውን በውል የምንገነዘብ እና የምንተገብር መሪዎች ነን- ይርጋ ሲሳይ

የዛሬውን በውል የምንገነዘብ እና የምንተገብር መሪዎች ነን- ይርጋ ሲሳይ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተሰበሰበ ካለው የሰሊጥ ሰብል ከ602 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

በማዕከላዊ ጎንደር ዞን እየተሰበሰበ ካለው የሰሊጥ ሰብል ከ602 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት እንደሚጠበቅ ተገለፀ

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልኩ ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለፀ

የፋይዳ ዲጂታል መታወቂያ ከነገ ጀምሮ በዘመቻ መልኩ ምዝገባ እንደሚካሄድ ተገለፀ

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?