፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 29 2017| NBC ETHIOPIA- አሜሪካ ውስጥ ከደርዘን በላይ የሆኑ ግዛቶች ቲክቶክን ህጻናትን ሱስ በማስያዝና የአእምሮ ጤናቸውን በመጉዳት ተከሰሰ።
ክሱ የተመሰረተው ከበርካታ የአሜሪካ ግዛቶች የተውጣጡ አቃቤ ህጎች ቲክቶክ ላይ ላለፉት ሁለት አመታት በህብረት ምርመራ ካደረጉ በኋላ ነው።

ክሱ በዋነኛነት የቲክቶክ አልጎሪዝም ላይ ያተኮረ ሲሆን ይህም ተጠቃሚዎች መተግበሪያው ውስጥ የሚያዘወትሯቸውን አይነት ቪዲዮዎች በማቅረብ ህጻናት የመተግበሪያው ሱሰኞች እንዲሆኑ የሚያደርግ ሲሆን ይህም የአእምሮ ጤናን በእጅጉ የሚጎዳ ነው ሲሉ ከሰዋል።
“ቲክቶክ የህጻናት ጤናማ አስተዳደግ መስዋእት እያደረገ ለትርፍ ብቻ እየሰራ ነው፤ ይህንን ደግሞ አንታገስም።” ሲሉ የካሊፎርኒያ ግዛት ጠቅላይ አቃቤ ሆግ ስለጉዳዩ በሰጡት ጋዜጣዊ መግለጫ ተናግረዋል።
በ-ዳንኤል መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












