፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 28 2017| NBC ETHIOPIA-ሰሜን ኮሪያ በቆሻሻ የተሞሉ ባሉኖችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ተሰምቷል፡፡
የደቡብ ኮሪያ ጦር ሀይል በሰጠው ማብራሪያ ሰሜን ኮሪያ ለሁለተኛ ተከታታይ ቀናት በቆሻሻ የተሞሉ ባሉኖቿን ወደ ደብብ ኮሪያ ምድር መላኩን አስታውቋል፡፡
የደብብ ኮሪያ ጦር ሀይል ለሀገሪቱ ዜጎች ፈፅሞ እነዚህን ባሉኖች እንዳይነኳቸው አስጠንቅቋል ፡፡
ሰሜን ኮሪያ ከባለፈው ግንቦት ወር ወዲህ ብቻ ከአምስት ሺ በላይ በቆሻሻ የተሞሉ ባሉኖችን ወደ ደቡብ ኮሪያ መላኳ ይነገራል፡፡
የደቡብ ኮሪያ የጦር ሀይል ባወጣው መግለጫ ሰሜን ኮሪያ ሁሉንም መስመር እያለፈች ነውና የማያዳግም እርምጃ እወስዳለሁ ሲል ነው ያስጠነቀቀው ዘገባው የዩናፕ ኒውስ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












