፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 28 2017| NBC ETHIOPIA- 5ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር “የቁልፍ መሠረተ-ልማት ደህንነት ለዲጂታል ሉዐላዊነት” በሚል መሪ ቃል ከጥቅምት 1/2017 እስከ ጥቅምት 30/2017 ዓ.ም እንደሚከበር የኢንፎርሜሽን መረብ ደህነነት አስተዳደር ገለፀ።
5ኛዉ ሀገር አቀፍ የሳይበር ደህንነት ወር የመክፈቻ ፕሮግራም ጥቅምተ 1/2017 ዓ.ም በሳይንስ ሙዚየም የሀገሪቱ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣናት፣ መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ተቋማት፣ የፋይናንስ ተቋማት፣ የሳይበር ቴክኖሎጂ ኩባንያዎች እና ሌሎችም በተገኙበት ይከፈታል ተብሏል።

በመርሃግብሩ የማህበረሰቡንና የተቋማትን የሳይበር ደህንነት ግንዛቤ ለማሳደግ የሚረዱ ሁነቶች እንደሚከናወኑም የኢንፎርሜሽን መረብ ደህንነት አስተዳደር ዋና ዳይሬክተር ትዕግስት ሃሚድ ገልፀዋል።
በ-ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












