፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 16 2017| NBC ETHIOPIA-በኮልፌ ቀራንዮ ክፍለ ከተማ ወረዳ 10 ከአባጃሌ- ልኳንዳ ያለው የውስጥ ለውስጥ መንገድ ለበርካታ ወራት የታክሲ አገልግሎት በመቋረጡ የመልካም አስተዳደር ችግር ሆኖ በማህበረሰብ ዘንድ ቅሬታ ሲነሳበት ቆይቷል፡፡

በክፍለ ከተማው የወረዳ 10 አስተዳደር ከከተማው ትራንስፖርት ቢሮ ጋር በመተባበር ከአባጃሌ- ልኳንዳ 3 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር ርቀት ያለው የውስጥ ለውስጥ መንገድ በዛሬው ዕለት የታክሲ ትራንስፖርት አገልግሎት እንዲጀመር አድርገዋል። በአገልግሎቱ መጀመር ከአካበቢው ማህበረሰብ በተጨማሪ የፌደራል ፓሊስ ጀግኖች ማገገሚያ ማዕከል ተገልጋዮችና ሰራተኞች ተጠቃሚዎች መሆናቸውን ከወረዳው ኮሙኒኬሽን ያገኘነው መረጃ ያመለክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












