፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 18 2017| NBC ETHIOPIA-አፍሪካ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የፀጥታው ምክር ቤት ቋሚ ውክልና ሊኖራት እንደሚገባ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ገለጹ።
አምባሳደር ታዬ በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 79ኛው የተመደ ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ንግግር አድርገዋል።
አምባሳደር ታዬ በኒውዮርክ እየተካሄደ ባለው 79ኛው የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ጠቅላላ ጉባኤ ላይ ባደረጉት ንግግር፣ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት ወቅቱን የሚመጥን ማሻሻያ እንደሚያስፈልገው ተናግረዋል።
አፍሪካ በተመድ የፀጥታ ምክር ቤት ቋሚ ውክልና አለማግኘቷ ኢ ፍትሐዊና ተቀባይነት የሌለው ነው ብለዋል።
ስለሆነም ምክር ቤቱ ለአፍሪካ በምክር ቤቱ ቋሚ ውክልና በመስጠት ፍትሐዊነትን እንዲያሰፍን ጠይቀዋል። ኢትዮጵያም የአፍሪካ የጋራ አቋም የሆነውን ውክልና ማግኘት ጉዳይ እንደምትደግፍ ተናግረዋል።
የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የተፋሰሱን አገራት በጋራ የማደግና የመበልፀግ ሕልም እውን የሚያደርግ ነው ያሉት አምባሳደር ታዬ፣ አምባሳደር ታዬ አጽቀሥላሴ ማዕቀፉ ወደ ትግበራ ምዕራፍ ሊገባ መቃረቡን ገልጸዋል።
ስምምነቱ ፍትሐዊ እና ምክንያታዊ የውሃ ሀብት አጠቃቀምን የሚያሰፍን ነው ብለዋል። የናይል የትብብር ማዕቀፍ ስምምነት የተፋሰሱን አገራት በጋራ የማደግ እና የመበልፀግ ሕልምን እውን የሚያደርግ ታሪካዊ ማዕቀፍ መሆኑን ገልጸዋል።
ስምምነቱን ያልፈረሙ አገራት ስምምነቱን በማፅደቅ ለማዕቀፉ ውጤታማነት ድጋፍ እንዲያደርጉ ጥሪ አቅርበዋል።
የዓባይ ግድብ ግንባታ ከኢትዮጵያ የኢነርጂ ኃይል የማግኘት ፍላጎትና በቀጣናው ካለው የኤሌክትሪክ ኃይል አቅርቦት መሻት የመነጨ ነው ብለዋል። በቀጣናው ትስስርና ትብብርን የማጎልበት ጉልህ ፋይዳ እንዳለው ገልጸዋል ሲል ኢዜአ ዘግቧል።
ኢትዮጵያ በጠቅላላ ጉባዔው ብሔራዊ ጥቅሞቿን በሚያስጠብቁ ጉዳዮች ላይ ጠንካራ ተሳትፎ እያደረገች ይገኛል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












