፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2017| NBC ETHIOPIA-የ2017 ዓ.ም የደመራ በዓልን አስመልክቶ በመስቀል አደባባይ የጽዳት ዘመቻ ተካሂዷል።
የጽዳት ዘመቻው “ክብረ በዓላቶቻችን የአብሮነታችንና የወንድማማችነታችን መገለጫ ተምሳሌቶቻችን ናቸው” በሚል መሪ ቃል ነው የተካሄደው።

በመርኃግብሩ የከተማዋ ነዋሪዎች ለበዓዐሉ በጋራ ዝግጅት ሲያደርጉ መቆየታቸው የተገለፀ ሲሆን ከመስቀል በዓል ማግስት ለሚከበረው የኢሬቻ በዓልም አብሮነቱ ተጠናክሮ እንዲቀጥል ጥሪ ቀርቧል።

በመርኃግብሩ የከተማ አስተዳደሩ ከፍተኛ አመራሮች፣ የተለያዩ የሃይማኖት አባቶች፣ የኪነ ጥበብ ባለሙያዎች፣ ወጣቶች እና የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ተገኝተዋል።
በ-ሊያ ክብሮም
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












