፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 15 2017| NBC ETHIOPIA- በቴላቪቭ አቅራቢያ በሚገኘው የሞሳድ የስለላ ተቋም ላይ ጥቃት መሰንዘሩን ሄዝቦላህ አስታውቋል፡፡ ነገር ግን ከቴላቪቭ ባለሰልጣናት ስለ ጉዳዩ የተሰተጠ አስተያየት የለም ተብሏል፡፡
ሄዝቦላህ፤በእስራኤል ጦር ለተገደለው ወታደዊ አዛዡ ኢብራሂም ቁባይሲ እና በመገናኛ መሳሪያዎች ላይ ለደረሰበት ጉዳት የበቀል ምላሽ መሆኑን ነው የገለጸው፡፡
ኢብራሂም ቁባይሲ የሄዝቦላህን የሚሳኤልና ሮኬት መሳሪያዎችን የሚያስተባብርና የሚመራ እንደነበር ታውቋል፡፡
በሌላ በኩል የእስራኤል ጦር በጋዛ በፈጸመው የአየር ጥቃት በራፋህ አካባቢ አንዲት እናትና አራት ልጆቿ መገደላቸው ሲገለጽ፤ በዌስት ባንክ ሄብሮን ደግሞ ስድስት ፍልስጤማውያን ተይዘዋል ሲል ዘ ኒው አረብ ዘግቧል፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












