፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 14 2017| NBC ETHIOPIA-በቀጣይ ሀሙስ የሚከበረው የ2017 ዓ.ም የመስቀል ደመራ በዓል የለ ምንም የጸጥታ ችግር በሰላም እንዲከበር የሁሉም አካላት ድርሻ መሆኑ ተገለፀ ።
የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ከአዲስ አበባ የሀይማኖት ተቋማት ጉባኤ ጋር በመሆን በመስቀል ደመራ በዓል አከባበር ዙሪያ የማጠቃለያ የምክክር መድረክ አካሂዷል።

የደመራ በዓል ከምንጊዜውም በላይ በመስቀል አደባባይ ጨምሮ በሁሉም አብያተ በቤተክርስቲያናት በድምቀት ለማክበር በቂ ዝግጅት መደረጉ በመድረኩ ተገልጿል ።
የሀይማኖት አባቶች ፣የሰንበት ትምህርት ቤት አገልጋዮች እና መላው የከተማዋ ነዋሪዎች የመስቀል ደመራ በዓል በሰላም እንዲከበር ሀላፊነታቸውን እንዲወጡ የአዲስ አበባ ሰላም እና ጸጥታ አስተዳደር ቢሮ ሀላፊ አሳስበዋል ።

በመድረኩ የአዲስ አበባ ሀገረስብከት ሊቀ ጳጳስ አቡነ ሔኖክ ጨምሮ በርካታ የሀይማኖት አባቶች ተገኝተዋል ።
በ- ሰላማዊት ወ/ገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












