፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 13 2017| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ አእምሯዊ ንብረት ባለስልጣን እና የቻይና ብሄራዊ አእምሯዊ ንብረት አስተዳደር በትብብር ለመስራት ያላቸውን ስምምነት በማጠናከር በቀጣይ ሁለት ዓመታት በተለያዩ አእምሯዊ ንብረት መስኮች ተግባራዊ የሚያደረጉትን እቅድ ማስፈፀሚያ ስምምነት አድርገዋል፡፡
ስምምነቱን የባስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ወልዱ ይመስል እና የአስተዳደሩ ኮሚሽነር ሼን ቻንግዩ መስከረም ባለፈው ሳምንት በቤጂንግ ተፈራርመዋል፡፡ ሁለቱ ሃገራዊ ተቋማት በአእምሯዊ ንብረት ዘርፍ ያላቸው የሁለትዮሽ ስምምነት ተግባራዊ በማድረግ ሂደት ስኬታማ ስራዎች የተከናወኑ መሆናቸውና አሁንም በኢትዮጵያና በቻይና መንግስታት መካከል በኢኮኖሚ ፣ በንግድ እና በተለይም በሳይንስና ቴክኖሎጂ መስኮች እየጎለበት የመጣውን ትብብር በአእምሯዊ ንብረት ዘርፍም አጠናክሮ ለመቀጠል የሚያስችል መሆኑ ተገልጿል፡፡

ስምምነቱ ኢትዮጵያ የብሪክስ ቡድን አባል ሀገራትን በተቀላቀለችበት ማግስት የተከናወነ በመሆኑም የተቋማቱን ትብብር ከፍ እንዲል እንደሚያስችለውና የሀገራችንን የአእምሯዊ ንብረት ጥበቃ ስርዓት ለማሰደግና ለማጠናከር ከፍተኛ ኣስተዋፅኦ እንዲሚኖረው የሃገራቱ ተቋማት ኃላፊዎች አረጋግጠዋል፡፡
ስምምነቱ የባለስልጣን መስሪያ ቤቱን የሰው ሃይል አቅም ለማሳደግ የሚያስችሉ የትምህርትና ስልጠና ዕድሎችን በቻይና ዩኒቨርስቲዎች የመስጠት፤ የመረጃ፣ የህግ፣ ቴክኒክ እና ተያያዝ ጉዳዮችን ያካተተ መሆኑን ለመገንዘብ ተችሏል፡፡
ከዚሁ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ በወቅቱ በተካሄደው ሶተኛው የቤልትእና መንገድ /BELT and ROAD/ ተባባሪ ሃገራት የአእምሯዊ ንብረት ተቋማት ኃላፊዎች ኮንፍረስ የተካሄደ ሲሆን ተሳታፊ ሀገራት በትብብር ሂደቱ ያስመዘገቡትን ስኬትና ቀጣይ የትብብር መስኮች ላይ ሰፊ ውይይት በማድረግ በቀጣይ የሚከናወኑ ተግባራት ላይ ስምምነት ላይ ደርሰዋል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbcv
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












