፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 08 2017| NBC ETHIOPIA-የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ከአማራ ልማት ማህበር ጋር በመተባበር በሰሜን ጎንደር ዞን በጠለምት ወረዳ በመሬት መንሸራተት ምክንያት ለተጎዱ ወገኖች 13 ሚሊዮን ብር የሚያወጣ ልዩ ልዩ አልባሳትን ድጋፍ አድርጓል።
የአማራ ልማት ማህበር ከሚያከናውናቸው የልማት ሥራዎች በተጨማሪ በተፈጥሮና ሰው ሠራሽ አደጋዎች ምክንያት ጉዳት ለደረሰባቸው የኅብረተሰብ ክፍሎች ድጋፍ እያሰባሰበ ይገኛል ያሉት የአማራ ልማት ማህበር ምክትል ስራ አሥፈጻሚ መዝገቡ አንዷለም፤ በቀጣይም በጎ አድራጊ አካላትን በማስተባበርና በማፈላለግ ተጨማሪ ድጋፎችን ያደርጋል ብለዋል፡፡
የአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን ምክትል ኮሚሽነር ሰርካዲስ አታሌ በበኩላቸው፤ ድጋፍ ያደረጉ ድርጅቶችን በማመስገን በሰሜን ጎንደር ዞን በመሬት መንሸራተት አደጋ ምክንያት ከ2 ሽህ 400 በላይ የሚሆኑ የህብረተሰብ ክፍሎች ከቀያቸውዉ ተፈናቅለው እንደሚገኙ ገልጸዋል፡፡

በመንግስት በኩል ከ500 በላይ ኩንታል የምግብ እህል በዚሁ ዞን ለሚኖሩና ለችግር ለተጋለጡ ወገኖች ከዚህ በፊት መስጠት እንደተቻለም አስረድተዋል፡፡
ከክልሉ ዉጭ ተፈናቅለዉ የመጡ ወጎኖችን በዘላቂነት ለማቋቋም ዕቅድ ታቅዶ እየተሰራ እንደሚገኝ የገለጹት ምክትል ኮሚሽነሩ፤ ዘላቂ መፍትሔ ለመስጠት ከባለድርሻ አካላት ጋር በቅንጅት እየተሰራ እንደሆነም አክለዋል፡፡
መንግስታዊና መንግስታዊ ያልሆኑ ድርጅቶች፣ ባለሃብቶች እና በመላው ዓለም የሚገኙ ኢትዮጵያዉያን በሙሉ ድጋፍ እንዲያደርጉም ጥሪ አቅርበዋል።
በአማራ ክልል በሰው ሠራሽ እና በተፈጥሮ አደጋዎች ምክንያት ከ589 ሺህ በላይ የሚሆኑ ተፈናቃዮች በተለያዩ መጠለያ ጣቢያዎች እና በማህበረሰቡ ዉስጥ በአስቸጋሪ ሁኔታ ተጠልለዉ እንደሚገኙ ከአማራ ክልል አደጋ መከላከልና ምግብ ዋስትና ኮሚሽን የተገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv





See insights
Boost a post
Like
Comment
Send
Share












