፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 07 2017| NBC ETHIOPIA- አሜሪካ የባላንጣነት ስሜቷን የምታቆም ከሆነ የቀጥታ ድርድር ማድረግ ይቻላል ስትል ኢራን አስታውቃለች፡፡
የኢራኑ ፕሬዚዳንት ማስዑድ ፔዜሽኪያን በሰጡት ማብራሪያ አሜሪካ የጠላትነት ግብሯን ርግፍ አድርጋ የምታቆም እና የምትታቀብ ከሆነ ኢራን በቀጥታ ለመደራደር ዝግጁ ናት ያ ደግሞ ጠላትነትን የሚያርቅ ነው ሲሉ ገልጸዋል።
ፔዜሽኪያን በዝርዝሩ መግለጫቸው አሜሪካውያን ወንድሞቻችን ናቸው ተንኮላቸውን የሚያቆሙ ከሆነ ሁሉም ሠላማዊና ቀና ይሆናል ነው ያሉት።
ከዚያም ውጪ የኢራኑ ፕሬዚዳንት ኢራን በአሜሪካ አቅራቢያ የወታደራዊ ማዘዣዎችን አትገነባም ብለዋል። ኢራን ለሩሲያ የባለስቲክ ሚሳይሎቿን ሰጥታለች የሚባለውም ክስ ቢሆን እኔ ወደ ሥልጣን ከመጣሁ ወዲህ አልተደረገም ሲሉ አስታውቀዋል ዘገባው የዳውን ነው።
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












