፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 06 2017| NBC ETHIOPIA-የቱሪዝም ሚኒስቴር የዓለም የቱሪዝም ቀን ከመስከረም 7 እስከ 9 ቀን 2017 ዓ.ም በኢትዮጵያ በተለያዩ ሁነቶች እንደሚከበር አስታውቋል፡፡
ሚኒስቴሩ ከምስራቅ አፍሪካ የልማት በይነ መንግስታት ባለስልጣን (ኢጋድ) እና ከተባበሩት መንግስታት የአፍሪካ ኢኮኖሚክ ኮሚሽን ጋር በመተባበር ቀኑን በማስመልከት በአድዋ ድል መታሰቢያ ሁነት ማዘጋጀቱን ጠቁሟል።
በሁነት ዝግጅቱ የኢትዮጵያ የቱሪዝም ሳተላይት አካውንት ይፋ እንደሚሆንም አመልክቷል።የተለያዩ የኢጋድ አባል ሀገራት፣ ክልሎች እና የቱሪዝም ተዋንያን የሚሳተፉበት “Origins travel market” የተሰኘ ኤግዚብሽን እንደሚካሄድ ተጠቅሷል።
የምስራቅ አፍሪካ የ10 ዓመት የቱሪዝም ማስተር ፕላን ይፋ ይሆናል ተብሏል።በዝግጅቱ ላይ ለመሳተፍ የኢጋድ አባል ሀገራት የቱሪዝም ሚኒስትሮች ጨምሮ ከ100 በላይ ልዑካን ወደ ኢትዮጵያ እንደሚመጡ ነው ሚኒስቴሩ ያስታወቀው።
ዜጎች ኤግዚቢሽኑን እንዲጎበኙና በሁነቶቹ ላይ እንዲሳተፉም ጥሪ ቀርቧል። የዓለም የቱሪዝም ቀን እ.አ.አ ከ1980 አንስቶ መስከረም 17 እየተከበረ ይገኛል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook – https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












