፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 03 2017| NBC ETHIOPIA- የስራና ክህሎት ሚኒስትር ሙፈሪሃት ካሚል ኢትዮጵያ ከዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት(World Skills) የሙሉ አባልነት ሰርተፊኬት መቀበሏን ገለጹ
ኢትዮጵያ የአለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት አባል መሆኗ በርካታ ፋይዳዎች እንዳሉት ሚኒስትሯ በማህበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት ገልጸዋል።
ከተለያዩ ሀገራት ጋር የኢንዱስትሪ ትስስር መፍጠር፣ በክህሎት ልማት ከተቀረው የዓለም ክፍል ልምድ በመለዋወጥ እንዲሁም በርካታ ፖለቲካዊ፣ ኢኮኖሚያዊና ማህበራዊ ልምዶችን መቅሰም እንደሚያስችል አመልክተዋል።

ይህም በዘርፉ እየተከናወነ ባለው ሥራ የተሻለ ለውጥ ለማምጣትና ከተቀረው የዓለም የክህሎት ልቀት ጋር እኩል ለመራመድ ሰፊ ምህዳር እንደሚፈጥር ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ የዓለም አቀፉ የክህሎት ድርጅት አባል መሆን በፈረንሳይ ሊዮን እየተካሄደ በሚገኘው የዓለም የክህሎት ውድድር ላይ ለመሳተፍና ከዓለም ጋር እርምጃዋን ለማስተካከል አግዟታል ነው ያሉት ሚኒስትሯ።
የድርጅቱ አባል መሆን ትልቅ የስኬት በር ከፋች እንደሚሆንም አመልክተዋል።ዓለም አቀፉ የክህሎት ውድድር ጳጉሜን 5 ቀን 2016 ዓ.ም የተጀመረ ሲሆን እስከ መስከረም 5 ቀን 2017 ዓ.ም ይቆያል።
ኢትዮጵያ በሁለቱም ጾታዎች በሶስት ክህሎት ዘርፎች (ICT and Networking, CNC Machine, Furniture Making ) ተወክላ ውድድሩ ላይ እየተሳተፈች ትገኛለች።በውድድሩ ላይ ከ70 ሀገራት የወጣጡ 1 ሺህ 400 ወጣቶች ተሳታፊ ሆነዋል።
ወጣቶቹ የተለያዩ የክህሎትና የፈጠራ ስራዎቻቸውን በማቅረብ ውድድራቸውን በማድረግ ላይ ናቸው።
የውድድሩ አላማ በየጊዜው እየተለወጠች ባለችው ዓለም የቴክኒክና ሙያ ተቋማት ያላቸውን ወሳኝ ሚና ማሳየት መሆኑም ተገልጿል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












