፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | መስከረም 03 2017| NBC ETHIOPIA-የእስራኤል ልዩ ሀይሎች በሶሪያ የኢራን የጦር መሳሪያ ማከማቻን ስፍራ መወረራቸው ተገልጿል ፡፡
የእስራኤል የጦር አውሮፕላኖች በዚህ ሳምንት በሶሪያ የሚገኘውን የኢራን አብዮታዊ ዘብ ሀይል የጦር መሣሪያ ዋና ማከማቻ ስፍራ ወርረው በርካታ የጦር መሳሪያና ሌሎች ምስጢራዊ ቁሳቁሶችን መውሰዳቸው ተገልጿል፡፡
የእስራኤል ኮማንዶዎች ከሄሊኮፕተር እየዘለሉ ኢራናውያኑን ለመያዝና አንዳንድ ጠቃሚ መረጃዎችን ለማግኘት ብርቱ ጥረት ካደረጉ በኃላ ስፍራውን ማውደማቸው ተገልጿል፡፡
እስራኤል በዚሁ ሳምንት በሶሪያ ምድር ዘልቃ በፈፀመቸው ከባድ የአየር ጥቃት አስራ ስምንት ሰዎችን መግደሏና ከአርባሶስት በላይ ሰዎችን ማቁሰሏ ይታወቃል ዘገባው የታይምስ ኦፍ እሰስራኤል ነው፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












