፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 05 2016| NBC ETHIOPIA- የጎንደር ከተማ አስተዳደር አዲሱን ዓመት ምክንያት አድርጎ ከ500 በላይ ለሚሆኑ የከተማዋ ነዋሪዎች ድጋፍ አድርጓል፡፡
የጎንደር ከተማ አስተዳደር ምክትል ከንቲባ ደብሬ የኋላ ከተማ አስተዳደሩ በዓልን ድጋፍ ከሚሹ የኅብረተሰብ ክፍሎች ጋር በአብሮነት ለመዋል ከባሕር ዳር በጎ አድራጎት ማኅበር በተገኘ የ450 ሺህ ብር ድጋፍ ከ500 በላይ ለሚሆኑ ነዋሪዎች የዓይነት ድጋፍ ማድረጉን ተናግረዋል።

ለመላው ኢትዮጵያዉያን እና ለከተማዋ ነዋሪዎች የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክትን ያስተላለፉት ምክትል ከንቲባዋ የከተማዋ ነዎሪዎች በዓልን ሲያከብሩ ድጋፍ ከሚያስፈልጋቸው የኅብረተብ ክፍሎች ጋር በአብሮነት እንዲሆን ጠይቀዋል።

አዲስ ዓመትን ተከትሎ ከተማ አስተዳደሩ ለ127 ተማሪዎች ከ600 በላይ ደብተርን ጨምሮ ሌሎች የትምህርት መሣሪያ ቁሳቁሶችን ድጋፍ አድርጓል።
ድጋፍ የተደረገላቸው የከተማዋ ነዋሪዎች ከተማ አስተዳደሩ ላደረገላቸው እገዛ ምስጋና ማቅረባቸውን አሚኮ ዘግቧል፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












