፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 05 2016| NBC ETHIOPIA- የሰሜን ኮሪያው መሪ ኪም ጆንግ ኡን ከአሜሪካ ጋር ለመዋጋት የኑክሌር ሀይላቸውን በከፍተኛ ደረጃ ማዘጋጀታቸው ነው የተገለፀው፡፡

ኪም በሰጡት ሰፊ ማብራሪያ ሀገራቸው የኑክሌር ጦር መሳሪያውዋን ቁጥርም ትጨምራለች ነው ያሉት፡፡ የሰሜን ኮሪያ መገናኛ ብዙኃን ባሰራጩት ዘገባቸው ፒዩንግ ያንግ የህዝቦቿን ሰላምና ሉዓላዊነቷን ለማስጠበቅ የኑክሬር ጦር መሳሪያዋን በተገቢው መንገድ በጠላቶቿ ላይ እንደምትጠቀም የሀገሪቱን ባለስልጣናት ጠቅሰው አሳይተዋል፡፡
የሰሜን ኮሪያው መሪ ይህንን መልዕክት ያስተላለፉት ደግሞ ሀገሪቱ የተመሰረተችበትን ጊዜ በማስመልከት ባደረጉት ንግግር ነው፡፡ ኪም በማጠቀለያ ንግግራቸውም አሜሪካ ና ተከታዮቿን ለመዋጋት ጠንካራ የጦር ሀይል ያስፈልጋል ሲሉ አሳስበዋል፡፡
በ- ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












