፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ጳጉሜ 04 2016| NBC ETHIOPIA- የትምህርት ሚኒስትር ብርሃኑ ነጋ (ፕ/ር) በ2016 ዓ.ም የትምህርት ዘመን የ12ኛ ክፍል መልቀቂያ ብሔራዊ ፈተና ከወሰዱ 684 ሺህ 205 ተማሪዎች ያለፉት 36 ሺህ 409 መሆናቸውን አስታወቁ፡፡
አዳሪ ትምህርት ቤቶች ከፍተኛ ውጤት ማስመዝገባቸውን በመግለጽ 1 ሺህ 363 ትምህርት ቤቶች ምንም ተማሪ አላሳለፉም ብለዋል፡፡
ፈተናውን ከወሰዱ ተማሪዎች መካከል ሀገራዊ አማካኝ ውጤት 29 ነጥብ 76 መሆኑን ጠቅሰው የዘንድሮው ከፍተኛ ውጤት ከ700 675 መሆኑን እና ይህም በሀገሪቱ ለመጀመሪያ ጊዜ የተገኘ ከፍተኛ ውጤት መሆኑን አስታውቀዋል እንዲሁም ከ600 ከተፈተኑት ውስጥ 575 ከፍተኛው ውጤት መሆኑን ጠቅሰዋል ዘገባው የፋና ብሮድካስቲንግ ኮርፖሬት ነው፡፡












