፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA-በዓለም ደረጃ በ2050 እንደ አዲስ በከተሞች የሚሰፍሩ ሰዎች ቁጥር 2.5 ቢሊዮን የሚደርስ መሆኑም ተጠቁሟል።
በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰፈራ ፕሮግራም ዳይሬክተር አና ክላውዲያ ሮዝፋክ እንደገለጹት በቀጣዮቹ ዓመታት በሚሊዮን የሚቆጠሩ የአፍሪካ ሀገራት ዜጎች በአዲስ መልኩ በከተማ የሚኖሩ በመሆናቸው አህጉሪቱ የውሃ አቅርቦት እና የኤሌክትሪክ ኃይል ተደራሽነት ላይ በይበልጥ መስራት ይጠበቅባታል ብለዋል።
ለዚህ ግዙፍ የሕዝብ ቁጥርም የአፍሪካ ሀገራት በቂ መኖርያ ቤቶችን የመሠረተ ልማት ስትራቴጂ እና ፖሊሲዎቻቸው ላይ ተግባራዊ ስራዎችን ማከናወን እንዳለባቸው ተናግረዋል ።
የአዲስ አበባ ከተማ ከንቲባ አዳነች አበቤ በበኩላቸው የአፍሪካ ከተሞች ልማትን ያስቀደሙ እና ውበትን የተላበሱ መሆናቸውን በመግለጽ በፎረሙ የታደሙትንም እንኳን ወደሁለተኛ ቤታችሁ አዲስ አበባ በሰላም መጣችሁ ብለዋል።
የከተማ እና መሠረተ ልማት ሚኒስትር ጫልቱ ሳኒ አዲስ አበባ ከተማ ለዜጎቿ ምቹ እና ጽዱ እንድትሆን ከተሞችን የማስፋፋት ስራው ተጠናክሮ እንደሚቀጥል ገልጸዋል።
በፎረሙ የተገኙት የአፍሪካ ሀገራት ተወካዮች አዲስ አበባ ከተማ ያሳየችውን ዘመናዊነት እና የከተማነት ለውጥንም አድንቀዋል።
በ-ፍቅረሚካኤል ዘየደ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












