፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA-የቀድሞው የአሜሪካ ፕሬዝዳንት ዶናልድ ትራምፕ ፕሬዝዳንት ሆነው ከተመረጡ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን እንደሚስቆሙት ተናገሩ።
አሁን ላይ ሪፐብሊካኑን ፓርቲ ወክለው ከምክትል ፕሬዝዳንት ካማላ ሃሪስ ጋር የምርጫ ፉክክር ላየ የሚገኙት ትራምፕ የሁለቱን ሀገራት ጦርነት ሊያስቆም የሚችል አስተማማኝ እቀድ አለኝ ብለዋል።
ከሌክስ ፈሪድማን ፖድካስት ጋር በነበራቸው ቆይታ ጦርነቱን ላይመለስ አስቆመዋለሁ ፤ይህንን እቀድ ለማስፈጸም ብዙ እርቅት እሄዳለሁ ሲሉ ነው የገለጹት ትራምፕ። እቀዴን ግን አሁን ለማንም አልሰጥም ፤ እቅዱን አሳልፌ ከሰጠሁ ተግባራዊ ሊሆን አይችልም ፤ የሚሳኩም አይሆኑም ፤ ይሄ ሰርፕራይዝ ነው ብለዋል።
ትራምፕ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነትን ለማስቀም እቅድ እንዳላቸው ብዙ ጊዜ ተመሳሳይ ሀሳብ ሲናገሩ ይህ የመጀመሪያቸው አይደለም ተብሏል።
የፕሬዝዳንቱ ሀሳብ ምርጫን አስታኮ መነገር የሌለበት ነው ሲል የሩሲያ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ከዚህ በፊት መተቸቱ ይታወሳል።
ከዚህ ጋር በተያያዘ በተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሩሲያ መልዕክተኛ ቫሲሊ ኔብኔንዚያ የሩሲያና ዩክሬን ጦርነት በአንድ ቀን የሚፈታ አይደለም ሲሉ የትራምፕን ሀሳብ ወረፍ አድርዋል ዘገባው ቲ አር ቲ ወርልድ ነው።
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












