፨ ፨ ፨ ፨ ፨፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 29 2016| NBC ETHIOPIA- የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ አገልግሎት የ2016 የበጀት አመት የእቅድ አፈጻጸም፣ የቀጣይ አመት እቅድና አዲሱን የአገልግሎት ታሪፍ ማሻሻያን አስመልክቶ መግለጫ በመስጠት ላይ ይገኛል።
የአገልግሎቱ ዋና ስራ አስፈፃሚ ሽፈራው ተሊላ በኤሌክትሪክ አገልግሎት ታሪፍ ላይ በየደረጃው ማሻሻያ መደረጉን ተናግረው የዋጋ ማስተካከያው ከመስከረም 1/2017 ጀምሮ ተግባራዊ እንደሚደረግ ገልፀዋል።
በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ አገልግሎትን ማግኘት የቻሉ ዜጎች 56 በመቶ ያህሉ ብቻ ሲሆን በ2030 ለሁሉም ዜጋ ተደራሽ ለማድረግ እቅድ መያዙንም ተናግረዋል።
በ2016 100 የገጠር ከተማና ቀበሌዎችን የኤሌክትሪክ አገልግሎት ተደራሽ ማድረግ መቻሉን የገለፁት ዋና ስራ አስፈፃሚው በቀጣይ አመት 200 የገጠር ከተሞችና ቀበሌዎች ተደራሽ ለማድረግ እቅድ ተይዟል ነው ያሉት።
ከ1 ሺህ በላይ በተቋሙ ሰራተኞችና አመራሮች ላይ ከብልሹ አሰራር ጋር በተያያዘ እርምጃ መወሰዱም ተገልጿል።
በ-አክረም ኑርያ
📌YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
📌 TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
📌Website – https://nbcethiopia.com/news/
📌Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
#NBC_ETHIOPIA
#ሆኖ_መገኘት












