፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 25 2016| NBC ETHIOPIA- የአዲስ አበባ ከተማ የደንብ ማስከበር ባለስልጣን በ2016 ዓ.ም ከህግ ተላለፊዎች ከ66 ሚሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን የገለጸ ሲሆን፤ ከኮሪደር ልማት ጋር በተያያዘ ደግሞ ህግ ጥሰዋል ከተባሉ ግለሰቦች በአንድ ወር ብቻ ከ25 ሚሊዮን ብር በላይ ተገኝቷል ብሏል፡፡

የደንብ ማስከበር ባለስልጣን ዋና ስራ አስኪያጅ ሻለቃ ዘሪሁን ተፈራ በ2016 ዓ.ም ከተከናወኑ ስራዎች መካከል በመሬት ማስከበር፤ 5 ሺህ 834 በቦታና ከ10 ሚሊዮን በላይ ካሬ መሬት ከደንብ ጥሰት ተጠብቀዋል ለልማት ውለዋል ብለዋል፡፡
ተቋሙ የ2016 ዓ.ም የእቅድ አፈፃፀም ሪፖርትን ባቀረበበት፣በገመገመበት እንዲሁም የ2017 ዓ.ም እቅዱ ላይ ከሚመለከታቸው ባለከድርሻ አካላት ጋር ውይይት ባደረገበበት መድረኩ 2016 ዓ.ም በርካታ ስኬታማ ስራዎች የተከናወኑበት እንደነበር ተናግሯል፡፡
በ2017 ዓ.ም የደንብ ማስከበር ሰራኞች አቅምን የማሰደግ፤ እንዲሁም ተቋሙ በሚሰራባቸው የደንብ ማስከበር ስራዎች የተሻለ የህግ ማስከበር ስራን ማከናወን የሚሉት ይገኙበታል፡፡
በ-ሰላም ይልማ












