፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 25 2016| NBC ETHIOPIA-የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ የ2016 ዓ/ም የዕቅድ አፈጻጸም ግምገማና የ2017 የበጀት የአመት የዕቅድ ትውውቅ መድረክ እየተካሄደ ነው።
ከተማዋን በኢንቨስትመንት ፣ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁት አቶ ባዩህ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ቢሰማሩ እምቅ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል ።
የጎንደር ከተማ ተቀዳሚ ምክትል ከንቲባ ባዩህ አቡሃይ በተጠናቀቀው በጀት ዓመት በኢንቨስትመንት ዘርፍ በርካታ ባለሀብቶች ኢንቨስትመንት ፍቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል፡፡ጎንደርን ኢንቨስትመንትን ፣ የቱሪዝም ማዕከል ለማድረግ በርካታ ስራዎች እየተከናወኑ መሆኑን የገለፁት አቶ ባዩህ ባለሀብቶች በተለያዩ የኢንቨስትመንት አማራጮች ቢሰማሩ እምቅ አቅም ያለው አካባቢ መሆኑን ገልጸዋል።

ከተማዋን ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት ማዕከል እናደርጋለን።ለጎንደር ኢንቨስትመንት አንዱ ማነቆ የውሃ አቅርቦት ሲሆን አሁን ላይ ችግሩን ለመፍታት መገጭ ግድብ በፍጥነት ለመጠናቀቅ እየተሰራ መሆኑን ገልጸዋል።
የመገጭ ግድብ ሲጠናቀቅ ለአግሮ ኢንዱስትሪ ዘርፍ ከፍተኛ አስተዋጽኦ መኖሩን ያነሱት አቶ ባዩህ ለሆቴል ቱሪዝም የመገጭ ግድብ መጠናቀቅ ትልቅ አቅም አለው።አግሮ ኢንዱስትሪ ፓርክ እየተገነባ መሆኑንም ጠቁመው ባለሀብቱ ፣የከተማው ነዋሪዎች የአካባቢን ሰላም ማስፈን ለኢንቨስትመንት ፍሰት የማይተካ ሚና አለው ብለዋል ።

ያሉን ዕድሎች ለመጠቀም ለአካባቢ ሰላም ልንሰራ ይገባል፤አሰራርን በማዘመን ኢንቨስትመንት ስራ ምቹ ሁኔታዎችን መፍጠር እንደሚገባ አሳስበዋል።በውጭም ሆነ በሀገር ውሰጥ ያሉ ባለሀብቶች በጎንደር ከተማ ኢንቨስት እንዲያደረጉ አቶ ባዩህ ጥሪ አቅርበዋል።
በምክትል ከንቲባ ማዕረግ የጎንደር ከተማ አስተዳደር ኢንዱስትሪና ኢንቨስትመንት መምሪያ ኃላፊ አቶ ግርማይ ልጃለም ዛሬን ሰርተን የነገዋን ጎንደር ብሩህ የምናደርግበት ስራ ልንሰራ ይገባል ።በተጠናቀቀው በጀት ዓመት 150 ቢሊዮን ብር ካፒታል ያስመዘገቡ 350 ባለሀብቶች ኢንቨስትመንት ፍቃድ መውሰዳቸውን ገልጸዋል ።
ለ101 ባለሀብቶች የኢንቨስትመንት ቦታ ማስተላለፍ ታቅዶ 100 ባለሀብቶች የተላለፈላቸው ሲሆን አፈጻጸሙ 99 በመቶ መሆኑን ተናግረዋል።የጎንደርን ኢንቨስትመንት ለማሳለጥ አጋር አካት በመደጋገፍ በመሰራት እንደሚገባ አቶ ግርማይ ገልጸዋል።
እንደ አማራ ኮሙኒኬሽን መረጃ በመድረኩ የከተማው ከንቲባ ባዩህ አቡሃይን ጨምሮ ሌሎች የከተማው ከፍተኛ አመራሮች ባለሀብቶችና ባለድርሻ አካላት ተገኝተዋል።












