፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 25 2016| NBC ETHIOPIA-7ኛው የሲቪል ምዝገባ እና ቫይታል ስታቲስቲክስ ቀን በሀዋሳ ከተማ እየተከበረ ይገኛል።በመርሃ ግብሩ ላይ የኢሚግሬሽንና ዜግነት አገልግሎት ዋና ዳይሬክተር ሰላማዊት ዳዊት የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ለሰላም መረጋገጥ ብሎም በኢኮኖሚ እድገት ላይ የላቀ አስተዋፅኦ እንደሚያበረክት ገልፀዋል።

በመሆኑም በፈረንጆቹ 2030 የልደት ምዝገባን ሙሉ በሙሉ የሞት ምዝገባን ደግሞ 80 በመቶ ለማከናወን እቅድ መያዙን ተናግረዋል።ከቀጣይ አመት 2017 ጀምሮ የአገልግሎት አሰጣጡን ለማዘመን የተለያዩ ማሻሻያዎች እንደሚደረጉም ዋና ዳይሬክተር አስረድተዋል።

አሁን ላይ ያለው የዜጎች የወሳኝ ኩነት ምዝገባ ዝቅተኛ መሆኑን የኢትዮጵያ ስታቲስቲክስ አገልግሎት ዋና ዳይቴክተር በከር ሻሌ ዶ/ር ጠቁመዋል።
ለዚህ የዜጎች የግንዛቤ ማነስን ጨምሮ አመራር ላይ የሚስተዋል ክፍተት በምክንያትነት ቀርበዋል።
በ-አክረም ኑርያ












