፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 17 2016| NBC ETHIOPIA-የፍትሕ ሚኒስትሩ ጌዲዮን ጢሞቲዮስ (ዶ/ር) በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ተገኝተው ከተማሪዎችና ከተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ጋር በመሆን የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራቸውን አሳርፈዋል።
በዚሁ ጊዜ ኢትዮጵያን አረንጓዴ የማልበሱ ስራ በሁሉም አካባቢዎች ባህል እየሆነ መምጣቱን ገልጸዋል።ሀገርን ለሚጠቅምና ለትውልድ የሚሻገር ስራ ላይ መተባበርና በጋራ መስራት ውጤቱ ያማረ መሆኑንም ተናግረዋል።
በዚህ ረገድ የአንድ ጀምበር አረንጓዴ አሻራ መርሃ ግብሩ ብዙዎች ሀገርን ለሚጠቅምና ለትውልድ የሚሻገር ስራ የመስራት ተነሳሽነት በተግባር የሚገለጥበት ነው ብለዋል።
እንዲህ አይነት ትብብርና የጋራ ዓላማ በሌሎች ስራዎች ላይም ተጠናክሮ እንዲቀጥል ሚኒስትሩ ጥሪ አቅርበዋል።
የጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር) ጥሪን ተከትሎ በርካታ ኢትዮጵያውያን ከማለዳው ጀምሮ ተከላው በሚካሄድባቸው አካባቢዎች አሻራቸውን ማኖር ጀምረዋል።












