፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 16 2016| NBC ETHIOPIA- የሱዳንን የእርስ በርስ ጦርነት ለማስቆም በአሜሪካ አደራዳሪነት በዚህ ሳምንት ካይሮ ላይ ሊደረግ የነበረው ስብሰባ ለሌላ ጊዜ መራዘሙ ተገለጸ፡፡
ድርድሩ የተቋረጠው የሱዳን መንግስት ተወካይ አለመላኩን ተከትሎ እንደሆነ የተገለጸ ሲሆን በአደራዳሪነት የተሰየሙት የአሜሪካው መልዕክተኛ ቶም ፕሪሎ ወደ ስዊዘርላንድ አቅንተዋል። ልዩ መልዕክተኛው በሱዳን እርዳታ በሚገባበት ጉዳይ ለመምከር ነው ወደ ስዊዘርላንድ የሄዱት፡፡
ከዚህ ጋር ተያይዞ በቻድ በኩል ወደ ዳርፉር የእርዳታ እህል የጫኑ ተሸከርካሪዎች እየገቡ መሆኑን መረጃዎች አመላክተዋል ፡፡
የሱዳን መንግስት በአሜሪካና በግብጽ ጋባዥነት በድርድሩ እንደሚሳተፍ አሳውቆ የነበረ ቢሆንም፤ አሁን ላይ አለመገኘቱ ታውቋል፡፡
የተለያዩ ዓለምአቀፍ ተቋማት የሱዳንን ጦርነት ለማስቆም እየወተወቱ እንደሆነ ቢታወቅም እስከሁን ግን ተጨባጭ እርምጃ ለመውሰድ አልተሳካላቸውም፡፡

የሱዳን የእርስ በርስ ጦርነት በሱዳን ህዝብ ላይ ሞት፤ ስድትና መፈናቀል ማስከተሉን ሱዳን ትሪቡን አስነበብቧል፡፡
በፈረንጆቹ ሚያዚያ 2023 ላይ ሳውዲ አረቢያና አሜሪካ በጅዳ ከተማ የሱዳን ተፋላሚ ሀይሎችን ወደ ድርድር እንዲመጡ ያደረጉት ጥረት አለመሳካቱ የሚታወስ ነው ፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












