Tuesday, November 17, 2026
  • Login
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
  • HOME
  • NEWS
  • PROGRAM AND FEATURES
    • HOLIDAY
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • CONTACT US
  • English
    • English
    • Amharic
No Result
View All Result
National Media
No Result
View All Result
Home News

በሕጻን ሄቨን ላይ ስለተፈፀመው ፀያፍ ወንጀል የምርመራ፣ ክስ እና ፍርድ ሂደት በተመለከተ ከአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ የተሰጠ አጭር ማብራሪያ፡-

August 20, 2024
in News
0 0
0
Share on FacebookShare on TwitterShare on Telegram

በቅድሚያ በልጃችን በሕጻን ሄቨን ላይ የተፈፀመውን አሰቃቂ፣ ከማኅበረሰቡ ባሕል እና ወግ ያፈነገጠ ፀያፍ ወንጀል ድርጊት እያወገዝን ሰሞኑን እናቷ ሲስተር አበቅየለሽ ሚዲያ ላይ ያደረገችውን ቃለ መጠየቅ እና የፍትሕ ጥያቄ መነሻ በማድረግ ድምጽ ለሆናችሁ፣ ትምህርት ለሰጣችሁ፣ ወንጀሉን እና ፈጻሚውን፣ በወንጀል ድርጊቱ እና ድህረ ወንጀል ተባባሪ ነበሩ በሚል ድርጊታቸውን ላወገዛችሁ አንቂዎች፣ ባለሙያዎች እና ታዋቂ ግለሰቦች ምሥጋናችን የላቀ መሆኑን እናሳውቃለን፡፡

ይህ ለፍትሕ ሲባል በቅንነት፣ ለሕግ የበላይነት በገባን ልክ ድምጻችንን ያሰማንበት እንደሆነ እንገነዘባለን፡፡ በተለይ ይህ ዓይነት ድምጽ ለፍትሕ ሥርዓቱ ጉልበት በሚሆንበት አግባብ በዕውነት በማስረጃ መሰጠት ሲችል ደግሞ ትርጉሙ ብዙ እንደሚሆን እናምናለን፡፡ ነገር ግን በስሜት ከወንጀሉ ዘግናኝ ባህሪ አኳያ ወይም የፍትሕ ተቋማት አሠራርን ሳንረዳ ወይም ሆነ ብለን ያንቋሸሽን ከሆነ ደግሞ ተገቢ አለመሆኑን እንድታውቁት ውጤቱ እና ተፅዕኖውም አሉታዊ መሆኑን ማስገንዘብ እንወዳለን፡፡ ስለሆነም የክልሉን መንግሥት አሠራር በማንቋሸሽ፣ የሕዝቡን ዕምነት እና ባሕሉን፣ የፍትሕ ተቋማት መልካም ስም በሚያጠፋ ሁኔታ ዘገባዎችን የሠራን ቆም ብለን እራሳችንን ልናይ እና ማስረጃን፣ ሁኔታን እና ምክንያትን እንድናገናዝብ አስፈላጊ ይሆናል፡፡

ስለሆነም ለመረጃ ይሆነን ዘንድ፣ ድጋፋችሁም መረጃን መሠረት አድርጎ፣ ዕውነትን በአረጋገጠ፣ ሕግን በጠበቀ ሁኔታ እንዲሰነዘር ፍላጎታችን መሆኑን በማመን በአማራ ክልል ፍትሕ ተቋማት ይህንን አሰቃቂ የወንጀል ድርጊት ተከትሎ ምን ተደረገ፣ ጉዳዩስ ምን ላይ ነው የሚለውን በተመለከተ አጭር መረጃ እንደሚከተለው መስጠት አስፈልጓል፡፡ ጉዳዩ በሕግ የመጨሻ ውሳኔ ያልተሰጠበት እና ውሳኔ የሚጠብቅ ስለሆነ ማንኛውም ጫና አሉታዊ ተፅዕኖ በፍርድ ቤቶች እንዳያሳድር በሚቻልበት ሁኔታ ድጋፋችሁን እንድታደርጉ መረጃው ጠቃሚነት እንዳለው ትረዱ ዘንድ መረጃ መስጠቱ አስፈልጓል፡፡

ድርጊቱ የተፈጸመው ሐምሌ 25/2015 ዓ.ም ነው፡፡ የድርጊቱ ቦታ ቀበሌ 14 ተብሎ ይጠራ ከነበረው አካባቢ ሲኾን ወቅቱ ሰላም የጠፋበት፣ መረጋጋት የሌለበት፣ ከፍተኛ በጦር መሳሪያ የተደገፈ ግጭት (ጦርነት) የነበረበት ወቅት ነው፡፡ ይህ ወቅት ብዙ ወንጀለኞች ግጭቱን እንደሽፋን በመቁጠር ብዙ ወንጀል ፈጽመውበታል፣ እራሳቸውን በግጭቱ ሸፍነው ብዙ አድርገዋል፡፡ በዚህ ወቅትም ልጃችን ሄቨን አንዷ የእነዚህ ግጭቱ ዕድል ለፈጠረለት ሰው ተጠቂ ሆናለች፡፡

ሕጻኗ ምን ሆነች፣ እንዴት ተገኘች፣ የት ተገኘች፣ ጉዳዩ ወደ ሕግ ቦታ እንዴት መጣ ሕጻኗ የተገኘችው ሻወር ቤት ውስጥ ነው፣ ስትገኝም ሕይወት ነበራት በሚባል ሁኔታ ላይ አይደለም፡፡ ፖሊስም ባለበት ከቦታው ወደ ሆስፒታል (መጀመሪያ የግል ጤና ተቋም)፣ ቀጥሎም የመንግሥት ሪፈራል ሆስፒታል ተወስዳለች፡፡ ሁለት ቦታ ምርመራ ተሠርቷል፡፡ ፖሊስ አብሮ በሂደቱ እና ሂደቱንም እየተከታተለ ስለነበር እና ሕጻኗ በተገኝችበት ቤት ሌላ ሰው አለመኖሩ ሲረጋገጥ ጥርጣሬውን ቤት ውስጥ ከነበረ ሰው ጋር አድርጎ ምርመራውን ቀጥሏል፡፡ በመኾኑም ይህ ፍርደኛ በቁጥጥር ስር ሊውል ችሏል፡፡

በምርመራው የአካባቢ ምስክር ድርጊቱን ያዬ ባለመኖሩ በቤት ውስጥ ሌላ ሰው አለመኖሩን እና በሕጻኗ አካል ላይ የደረሰውን ጉዳት የሕክምና ምርመራውን መሠረት አድርጎ ተካሂዷል፣ (ከ27 ጀምሮ በተለይ ባሕርዳር ከተማ ከፍተኛ ብጥብጥ እና ግጭት በመኖሩ በፖሊስ ቁጥጥር ስር የነበረው የአሁኑ ፍርደኛ ወጥቶ ነበር)፡፡ ከተማው ተረጋግቶ በቁጥጥር እስኪውልም በነጻነት ይንቀሳቀስ ነበር፡፡ (የህግ አስፈፃሚዎችም ሲስተር አበቅየለሽም በዚህ ሂደት ለጥቃት ተጋላጭ ነበሩ)፡፡

ስለሆነም በአስቸጋሪ ወቅት ግጭት በነበረበት ወቅት ሐምሌ 25/11/2015 ዓ.ም ጥቃቱ ተፈጽሟል፡፡

በፍትሕ ተቋማቱ (በፖሊስ፣ በጠቅላይ አቃቢ ሕግ እና በፍርድ ቤት ምን ተከናወነ ?)

1.ምንም እንኳ ወቅቱ አስቸጋሪ ቢሆንም የቅድሚያ ቅድሚያ ተሰጥቶ ተጠርጣሪው ወዲያው በቁጥጥር ስር ውሏል፡፡

2.ፖሊስ ጣቢያው በታጠቁ ኃይሎች ሲሰበር እና ሲዘረፍ መውጣቱን እና የተጎጅ ቤተሰብን፣ የሕግ አካላትን ሳይቀር ተጽዕኖ ለማድረስ ቢሞክርም ተመልሶ በፖሊስ ኃይል ለሕግ ቀርቧል፣ በቁጥጥር ስርም ውሏል፡፡

3.ምርመራው ተደርጎ በምርመራው እና ባሉት የሰው እና የሰነድ ማስረጃዎች መነሻነት ፍትሕን ለማረጋገጥ በሚያስችል ሁኔታ የሀገሪቱ አግባብ የሆነውን የወንጀል ሕግ አንቀጽ ተጠቅሶ ከፍተኛ ቅጣት በተደራራቢ ወንጀል ሁለት ክስ ማቅረብ ተችሏል፡፡

4.ክሶችም የግፍ ግድያ የወንጀል ሕጉ 539 እና በመድፈር መግደልን 620 (3) ያጣቀሰ ነበር፡፡ ይህም የሞት ፍርድ ወይም የዕድሜ ልክ እስራት ድረስ የሚያስቀጣ ነው፡፡

5.በክርክር ሂደት ተከሳሽ ክዶ ጠበቃ አቁሞ የተከራከረ ሲኾን ይህም ሕጋዊ አሠራር ነው፤ በክርክሩ የታዩ የሙያ ሥነ ምግባር ጉዳዮች ወይም ወንጀል ከተፈጸመ ማየቱ እና ተጠያቂነትን ማረጋገጥ እንደተጠበቀ ሆኖ፡፡

6.መጨረሻ ግራ ቀኝ ክርክሩን ሰምቶ የቀረበው ማስረጃ የግፍ ግድያን ሳይሆን (539) በመደፈር መሞቷን የሚያረጋግጥ መሆኑን በማረጋገጥ ተጠርጣሪው በ25 ዓመት ፅኑ እስራት ሊቀጣ ውሳኔ አርፎበታል፡፡ ስለሆነም ፍርደኛው አሁንም ማረሚያ ቤት ይገኛል፡፡

7.በአሁኑ ወቅት ፍርደኛው የፍርደኛ ይግባኝ አቅርቦ ጠቅላይ ፍርድ ቤት ጉዳዩን በመመርመር ላይ ይገኛል፣ ይሄም ሕጋዊ እና የተለመደ አሠራር ነው፡፡ ዐቃቢ ሕግ የስር ፍርድ ቤት የወሰነው የጥፋተኝነት እና የቅጣት ውሳኔ በሕጉ አግባብ መኾኑን ቢያንሰው እንጂ የሚበዛበት አለመኾኑን ከወንጀሉ አሰቃቂነት አኳያ በመግለጽ ፍርድ ቤቱ ፊት ቀርቦ አስረድቷል፡፡ ጉዳዩም ለውሳኔ ለሚቀጥለው ዓመት ተቀጥሮ አድሯል፡፡ አሁንም ፍትሕ ቢሮው ጉዳዩን በአግባቡ እየተከታተለው ይገኛል፡፡ ምናልባት ጠቅላይ ፍርድ ቤቱ የሚሰጠው ውሳኔ በአሉታዊ ቢኾን ለፌዴራል ጠቅላይ ፍርድ ቤት ይግባኝ በዐቃቢ ሕግ በኩል የሚቀርብ እንደኾነም ለማሳወቅ እንወዳለን፡፡

እንደመውጫ፡-

በሕጻናት ላይ የሚፈፀም ወንጀል በሀገር ላይ፣ በትውልድ ቀጣይነት ላይ፣ ሕግን ብቻ ሳይኾን ሰው መኾንን የተቃረነ አውሬነት መኾኑን አውቀን ልንዋጋው፣ ልናስቆመው የሚገባ ነው፡፡ ሕግን ብቻ ሳይኾን ፍትሕን፣ እኩልነትን፣ ሞራልን፣ ርትዕን በአጠቃላይ የተቃረነ ፀያፍ ወንጀል ሲኾን ሁላችንም በአንድነት በቅንጅት በእኩል ተቆርቋሪነት ልንታገለው ይገባል፡፡ ወደፊት የሕግ ማሻሻያ ሥራዎችንም ታሳቢ አድርገን ድምፃችንን ለመስጠት ዕድሉ አለ፡፡ በዲስፕሊን የሚታዩ ጉዳዮች፣ በወንጀል የሚያስጠይቅ በሂደቱ የተንፀባረቁ ጉዳዮች ካሉ በጥሞና (በጥቆማችሁ መነሻነት) ይታያሉ፡፡ ለሕግ፣ ለፍትሕ፣ ለርትዕ እንሠራለን!

ነፍስሽ ትረፍ ህጻን ሄቨን!!!

በቃ ይበለን!

የአማራ ክልል ፍትሕ ቢሮ ነሐሴ 14/2016 ዓ.ም

May be a graphic of text

See insights

Boost a post

Like

Comment

Send

Share

ShareTweetShare
Previous Post

“የዳኝነት አገልግሎቱን ፈጣን እና  ወጭ ቆጣቢ ለማድረግ  የተቋማቱን አሠራር በቴክኖሎጂ ማጠናከር ይገባል”-አቶ ዓለምአንተ አግደው

Next Post

ለአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጠንካራ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት

Related Posts

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ
Hard Talk

የትኩረት ማጣትና መቅበጥበጥ ተግዳሮቶች ፡ በዶክተር ዮሐንስ ባህረ ጥበብ

November 17, 2026
25
COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)
News

COP32 የኢትዮጵያን የአየር ንብረት አጀንዳ ለማራመድና ኢንቨስትመንትን ለመሳብ ትልቅ ዕድል ይፈጥራል- ጠቅላይ ሚኒስትር ዐቢይ አሕመድ (ዶ/ር)

November 16, 2026
9
መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!
News

መርካቶ የበጎነት መንደር፦ ማህበራዊ ፍትህ በተግባር፣ የዜጎች ሕይወት በእውነት ሲቀየር!

November 16, 2026
8
በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች
News

በ2026/27 የባርሴሎና እና የሪያል ማድሪድ ተቃራኒ ነጥቦች

November 16, 2026
16
ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ
Hard Talk

ህወሃት የሚመራው ጥምረት የፈረሰው የተቋቋመ ዕለት ነው! – የጠቅላይ ሚኒስትሩ የምስራቅ አፍሪካ ጉዳዮች አማካሪ ሚኒስትር አቶ ጌታቸው ረዳ

November 13, 2026
52
ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)
News

ኢትዮጵያ የቀይ ባህር ባይተዋር አይደለችም! – የመካከለኛው ምስራቅና ኤዢያ ፓስፊክ ጉዳዮች ከፍተኛ ተመራማሪ አንተነህ ጌታቸው (ዶ/ር)

November 13, 2026
38
Next Post
ለአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጠንካራ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት

ለአስገድዶ መድፈር ወንጀል ጠንካራ ቅጣት የሚጥሉ ሀገራት

የታይዋን እና ጃፓን ግንኙነት

የታይዋን እና ጃፓን ግንኙነት

ዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝን አስቀድሞ ለመከላከል እየተሰራ ነው -ጤና ሚኒስቴር

ዝንጀሮ ፈንጣጣ ወረርሽኝን አስቀድሞ ለመከላከል እየተሰራ ነው -ጤና ሚኒስቴር

Leave a Reply Cancel reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026
የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

የህወሓት አመራሮች ጦርነትን እንደ ጡረታ የሚያዩ ናቸው” – ጌታቸው ረዳ

November 17, 2026

Popular Posts

  • የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    የሆድ መነፋት ምንድ ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • አልማዝ ባለጭራ (Herpes zoster)

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • ሱስ ምን ማለት ነው?

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • በአለም ላይ ያሉ አስገራሚ ሁነቶች

    0 shares
    Share 0 Tweet 0
  • የ8ኛ ክፍል መልቀቂያ ፈተና ማለፊያ ውጤት ይፋ ተደረገ

    0 shares
    Share 0 Tweet 0

Follow Us:

Facebook Youtube
National Media

Follow Us:

Recent News

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

የቱሪዝም ዘርፉን ለማሳደግ የዲጂታል ቴክኖሎጂ አጠቃቀምን ማዘመን ያስፈልጋል ተባለ!

November 17, 2026
ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

ዓለም አቀፍ የባህል ማዕከላት በኢትዮጵያ

November 17, 2026

Company

  • About Us
  • Career
  • Advertising

Contact Us

Mesqel Square Road, Addis Ababa, Ethiopia.
+251 970707143
+251 970707142
Email: info@nbcethiopia.com

  • Apps
  • Terms & Policy

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

No Result
View All Result
  • Home
  • NEWS
    • NEWS SHOW
    • NEWS
    • NEWS PROGRAM
  • PROGRAM AND FEATURE
    • Holiday
    • NBC MAGAZINE
    • NBC REALITY SHOW
    • NBC TALK SHOW
    • NBC DOCUMENTARY
  • TV SERIES
    • NBC DRAMA
    • NBC SITCOM
    • NBC MOVIES
  • LIVE
  • English
    • English
    • Amharic

© 2024 - NBC ETHIOPIA. All Right Reserved.

Welcome Back!

Login to your account below

Forgotten Password?

Create New Account!

Fill the forms bellow to register

All fields are required. Log In

Retrieve your password

Please enter your username or email address to reset your password.

Log In

Add New Playlist

Are you sure want to unlock this post?
Unlock left : 0
Are you sure want to cancel subscription?