፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ነሐሴ 16 2016| NBC ETHIOPIA- የዝንጀሮ ፈንጣጣ በመላው አፍሪካ የሕብረተሰብ ጤና አደጋ መሆኑን የአፍሪካ በሽታዎች መቆጣጠሪያ እና መከላከያ ማዕከል (ሲዲሲ) ማስታወቁ ይታወሳል ።የጤና ሚኒስቴር በሽታው በኢትዮጵያ እስካሁን አለመከሰቱን ገልጾ በሽታው አስቀድሞ የመከላከል ስራዎች እየተሰሩ መሆኑ ለመገናኛ ብዙሀን በሰጠው መግለጫ አስታውቋል ። የበሽታው ምልክት በታየባቸው ሰዎች ላይ እስካሁን በተደረጉ ምርመራዎች በሽታው በኢትዮጵያ አለመከሰቱን የጤና ሚኒስትር ዶ/ር መቅደስ ዳባ ገልጸዋል ።
በአሁኑ ወቅት የተከሰተው በሽታው ወረርሽን ከዚህ በፊት ካጋጠሙት ወረርሽኞች ሁሉ የበለጠ አደገኛ መሆኑን የጤና ሚኒሰትር ዶ/ር መቅደስ ጠቁመው በተለይ ይህ ወረርሽኝ በአፍሪካ በ13 ሀገራት መከሰቱን ገልጸዋል ።
ይህ ወረርሽኝ በአጎራባች ሀገሮች መከሰቱን ተከትሎ ጤና ሚኒስቴር በቂ የቅድመ መከላከል ዝግጅት ማድረጉን እና በድንበር አከባቢዎችና በቦሌ አየር መንገድ ጊዚያዊ የመመርመርያ ጣቢያዎች መቋቋማቸው ገልጿል ። እንዲሁም የበሽታው ምልክት በሚታይባቸው ላይ አፋጣኝ ምርመራ ለማድረግ የሚያስችሉ ላብራቶሪዎች ተዘጋጅተዋል ተብሏል ። በተጨማሪ የህክምና ባለሙያዎች በበቂ ሁኔታ ማሰልጠን መቻሉን ተጠቁሟል።
በ-ሰላማዊት ወልደገሪማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCETHIOPIA
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












