፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 25 2016| NBC ETHIOPIA- ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር ተመስገን ጥሩነህ ከተምሳሌታዊዋ የምድር ጌጥ፣ ከተፈጥሮ ሀያል ግርማ ሞገስ ማሳያዋ ምድር ባህር ዳር መግባታቸውን ገለጹ፡፡
ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትሩ በማኅበራዊ ትስስር ገጻቸው ባሰፈሩት መልዕክት “ባህር ዳር ውብ ብቻ አይደለችም፤ ውበት ናት!” ብለዋል፡፡

ዛሬ በከተማዋ የሚገኘውን የባህር ዳር ስታዲየም ያለበትን ደረጃ መመልከታቸውን ገልጸዋል፡፡ስታዲየሙ አህጉራዊ እና ዓለም አቀፋዊ ውድድሮችን ማስተናገድ እንዲችል ተድረጎ እየተገነባ እንደሚገኝ ጠቁመዋል፡፡
በግንባታ ምዕራፍ የመጨረሻ ደረጃ ላይ የሚገኘው ስታዲየሙ በቀጣይ አመት ግንባታው ተጠናቆ ጨዋታዎችን ማስተናገድ እንዲችል ድጋፎች ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡


በቆይታቸውም በባህር ዳር ስታዲየም የአረንጓዴ አሻራ መርሀ ግብር ማካሄዳቸውን ገልፀው በባህርዳር አለም አቀፍ አውሮፕላን ማረፊያ ልባዊ አቀባበል ላደረጉላቸው የአማራ ክልል ከፍተኛ አመራሮች ብሎም ለከተማዋ ከንቲባ እና ህዝብ ላቅ ያለ ምስጋና አቅርበዋል።
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












