፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 25 2016| NBC ETHIOPIA- የዓለም የሳንባ ካንሰር ቀን በኢትዮጵያ ለመጀመሪያ ጊዜ በዓለምአቀፍ ደረጃ ለ13ኛ ጊዜ “ግንዛቤ ከመፍጠር ወደ ተግባር፤ የኢትዮጵያ የመጀመሪያ የዓለም የሳንባ ካንሰር ቀን” በሚል መሪ ቃል እየተከበረ ይገኛል።
ጤና ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያ ቶራሲክ ሶሳይቲ እና ማቲዎስ ወንዱ የኢትዮጵያ የካንሰር ሶሳይቲ በትብብር በሳንባ ካንሰር ላይ የተደረጉ ጥናቶች ውጤት የሚቀርብበት የውይይትና የግንዛቤ ማስጨበጫ መርሃ ግብር በማካሄድ ላይ ናቸው።
በካንሰር ምክንያት ከሚከሰት ሞት የሳንባ ካንሰር ቀዳሚውን ድርሻ ቢይዝም በበሽታው ህይወታቸውን የሚነጥቁ ዜጎችን ህይወት ለመታደግ የሚደረገው ጥረት በህክምና ተደራሽነት ችግር ሳቢያ ፈታኝ ስለመሆኑ በመድረኩ ተነግሯል።
የሳንባ ካንሰር ምጣኔ እየጨመረ ቢመጣም ከበሽታው ተጠቂዎች የህክምና አገልግሎት የሚያገኙት 15%ዎቹ ብቻ ናቸው ተብሏል።
የሳንባ ካንሰር በገዳይነታቸው እስከ አስር ከተቀመጡ በሽታዎች መካከል ቢሆንም በበሽታው ላይ የሚደረጉ የምርምር እና ጥናት ውጤቶች ውስንነት ስለመኖሩ ተገልጿል። የሰው ሃይል እጥረትም ሌላኛው ፈተና ነው ተብሏል።
የዓለም የሳንባ ካንሰር ቀን ህብረተሰቡ ስለሳንባ ካንሰር ያለውን ግንዛቤ ለማሳደግ እና በበሽታው ላይ የሚደረግ ምርምርን ለመደገፍ ያለመ ነው።
በኢትዮጵያ እየተከበረ የሚገኘው ቀኑ በብሪቶል ማየርስ ስኩዊብ ፋውንዴሽን (BMSF) ድጋፍ ኢትዮጵያ ላይ የሚተገበረው የሳንባ ካንሰር ፕሮጀክት አካል ነው።
በ-መቅደስ ደምስ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












