፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 25 2016| NBC ETHIOPIA- በእስራኤልና በሄዝቦላ መካከል ከተካረረው ውጥረት አንፃር ወደ ሊባኖስ የአየር በረራቸውን ያቋረጡ ሀገራት ዜጎቻቸው ሊባኖስን ለቀው ይወጡ ዘንድ አሳስበዋል፡፡
የእስራኤል ጦር ሀይል በሊባኖስ ዋና ከተማ ቤሩት ላይ ጥቃት ፈፅሞ የሄዝቦላውን ከፍተኛ መሪ ፋአድ ሹኩርን መግደሉን ተከትሎ አሜሪካ ዜጎቿን ወደ ሊባኖስ እንዳይጓዙ በጥብቅ አሳስባለች፡፡
ከዚያም ውጪ አሜሪካ በሊባኖስ ያሉ ዜጎቿ እንደሁኔታው ወደ ሚመች መጠለያ ለመጠጋት ያዘጋጁ ዘንድም ነው ትዕዛዝ የሰጠችው፡፡
የፍልስጤማውያኑ ተዋጊ አንጃ ከፍተኛ መሪው ኢስማይል ሀኒያ መገደላቸውን ከተነገረ ከሰዓታት በኃላ የሊባኖሱ ተዋጊ አንጃ ሄዝቦላም ከፍተኛ አዛዡ ፉአድ ሹኩር ከሌሎች አምስት ሰዎች ጋር መገደላቸው ተሰምቷል፡፡
ያንን ተከትሎም ውጥረቱ መካረሩ ሲነገር በሀኒያ ግድያ ዙሪያ ግን የእሰስራኤል መሪዎች የሰጡት ፍንጭ የለም ዘገባው የአሸርቅ አል አውስት ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












