፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 24 2016| NBC ETHIOPIA- የሱዳን ጦር ኃይሎች አዛዥ ጄኔራል አብደል ፋታህ አል-ቡርሃን ከግድ ሙከራ መትረፋቸው ተገለጸ፡፡
ጀነራሉ በምስራቃዊ የጦር ማዘዣ ላይ የሚገኙ ወታደሮችን ለማስመረቅ በነበሩበት ሰአት ነው የድሮን ጥቃት የተፈጸመባቸው የተባለው፡፡
ከፖርት ሱዳን 100 ኪ ሜ ርቆ በሚገገኘውና ጅቤት ተብሎ በሚጠራው የጦር ሰፈር ጥቃቱ የደረሰ ሲሆን አምስት ሰዎች መሞታቸው ታውቋል፡፡
የሱዳን ጦር ቃል አቀባይ በጄኔራል አል-ቡርሃን ላይ የግድያ ሙከራ የፈጸመው የፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ ነው ቢሉም የፈጥኖ ደረሽ ሀይሉ እጄ የለበትም ማለቱ ተሰምቷል፡፡
በሱዳን ጦርና በፈጥኖ ደራሽ ሀይሉ መካከል የተጀመረው ጦርነት ሱዳንን ከባድ ምስቅቅል ውስጥ እንድትገባ አድርጓታል ተብሏል፡፡ ዘገባው የሚድል ኢስት ሞኒተር ነው፡፡
በ-ቶማይ መኮንን
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












