፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
ሰዎች ለመዝናናት እና አዳዲስ ሁነቶችን ለመከወን በማህበራዊ ትስስር ገጾች በሚዘዋወሩ ምስሎች እና መረጃዎች ተመርኩዘው ስፍራዎችን መምረጥ እየተለመደ መጥቷል፡፡
እየተገባደደ ባለው የፈረንጆች 2024 በአለም ዙሪያ ለሚገኙ ጎብኚዎች ምርጥ የመዳረሻ ቦታ ናቸው ያላቸውን100 ስፍራዎች ታይም ይፋ አድርጎል ፡፡ ጥቂቶቹን እነሆ
Icon of the Seas መርከብ

ቫኬሽንን በተለየ የመርከብ ላይ ሽርሽር ላይ ማሳለፍ በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ እየሆነ መቷል፡፡ በሚአሚ የሚገኘው እና በአንድ ጊዜ 10 ሺ የሚጠጉ ሰዎችን የመያዝ አቅም ያለው Icon of the Seas መርከብ ለመርከብ ላይ ሽርሽር በበርካቶች ዘንድ ተመራጭ መዳረሻ መሆን ችሏል ፡፡ በውስጡም ለቤተሰብ የሚሆኑ ቅንጡ ማረፊያዎች ፤ ሰባት የዋና ገንዳ ፣ በውሃ ላይ የተሰራ ግዙፍ ወተር ፓርክ እና ቆይታን የሚያሳምሩ በርካታ መዝናኛ ስፍራዎች በውስጡ ይገኛሉ ፡፡ መርከቧም በየደረሰችበት ዳርቻዎች የሚከወኑ ሁነቶች በጎብኚዎች ዘንድ ተመራጭ መሆኑን የታደሙት ይመሰክራሉ፡፡ በዚህ የቱሪዝም ዘርፍ በ2023 31.7 ሚሊዮን ጎብኚዎች መመዝገባቸውን ታይም መጽሄት አስነብቧል፡፡
ለተፈጥሮ እና ውሃ አድናቂዎች የአይን ማረፊያ ናት ይባልላታል፡፡ በሜዲትራኒያን ባህር ላይ የምትገኘው የስፔኗ ፎርሜንቴራ ደሴት፡፡

ሰዎች በቀላሉ ዘና ለማለት እና መንፈሳቸውን ለማደስ ወደ ደሴቷ ያቀናሉ፡፡ ደሴቷ በአውሮፓ ከሚገኙ ውብ የባህር ዳርቻዎች ምርጧ በመባል ተመርጣለች፡፡
የጀልባ ሽርሽር እና በሚያብረቀርቅ ክሪስታል ውሃ ውስጥ መዋኘት በጎብኚዎቹ የሚከወኑ ተወዳጅ ተግባራት ናቸው፡፡ደሴቲቱንም ለመጎብኘት የበጋ ወቅት ተመራጭ ጊዜ ነው ተብሏል፡፡
በለምለም መልካምድሩ በሚታወቀው የአፍሪካ ትልቁ ተራራ ኪሊማንጃሮ የተከበበው የኬኒያው ቅንጡ አንጋማ አምቦሴሊ ሎጅ በ2024 ምርጥ ተጎብኚ ስፍራዎች ዝርዝር መካተት ችሏል፡፡

ሎጁ በሚገኝነት ብሄራዊ ፓረክ ውስጥ የሚገኙት እንደ ዝሆን ፣ አንበሳ፣ ነብር ፣ ጎሽ እና በርካታ ዝርያዎች ያላቸው የዱር እንስሳት እና ወፎች ጎብኚዎችን የሚያማልሉ ምስህቦች ናቸው፡፡
የእግር ጉዞ እና የተለያዩ እንቅስቃሴዎችን ማድረግ ፣የተለያየ ብዝሃ ህይወት መመልከት እና ፎቶ ማንሳት ወደ ቦታ ለሚያቀኑ ጎብኚዎች ተወዳጅ ድርጊቶች መሆናቸው ነው የተካተተው፡፡
በአሁን ወቅት ሰዎች ስለ ምድር እና ጠፈር እንዲሁም ሳይንሳዊ አወቃቀሮች ለማወቅ ያላቸው ጉጉት እየጨመረ መምጣቱ ይስተዋላል፡፡ከዚም ጋር ተያይዞ የጠፍር እና ተያያዥ ቱሪዝም ዘርፉ በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መሆኑን መረጃዎች ያሳያሉ፡፡ በዚ ቱሪዝም ዘርፉ ደግሞ ቻይና ተመራጭ መዳረሻ ናት ይለናል ሲ ኤን ኤን፡፡
ቻይና ይህን የቱሪዝም ዘርፍ ለማዳበር ያላት ፍላጎት ከፍተኛ ነው፡፡ የዌንቻንግ ከተማም የሮኬት ማስወንጨፊያ ማዕከል እና ከጠፈር ጋር የተያያዘ የቱሪዝም መዳረሻ በመሆን እያገለገለች ትገኛለች፡፡












