፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 17 2016| NBC ETHIOPIA-በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልል የተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎችን የወከሉ ተሳታፊዎች እና ባለድርሻ አካላት ያካተተው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ የምክክር ምዕራፍ በይፋ ተጀምሯል።
የኢትዮጵያ ሀገራዊ ምክክር ኮሚሽነር ዘገየ አስፋው በቤሻንጉል ጉሙዝ ክልል የሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰቢያ መርሀግብር 10 የማህበረሰብ ክፍሎችና ባለድሻ አካላት የተካተቱበት እንደሆነ ተናግረዋል።

እንደ ሀገር ያሉትን መሰረታዊ ችግሮችን በመለየት ለሀገራዊ ምክክሩ ለማቅረብ የሚያስችል ነው ብለዋል።
በክልሉ የሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብር ለሀገራዊ ምክክሩ አጀንዳ ለመስጠት ፤ ጥልቅ ውይይት በአጀንዳዎች ለማከንወን እንዲሁም ክልሉ በሀገራዊ ምክክሩ የሚወከሉ ተሳታፉዎችን የሚመርጡበት መድረክ እንደሚሆን ተጠቁሟል።
በክልሉ የሚደረገው የአጀንዳ ማሰባሰብ መርሃግብር ዛሬን ጨምሮ ለ6ቀናት የሚደረግ ነው።
በ-ሰላም ይልማ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Website – https://nbcethiopia.com/news/
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv




See insights and ads
Like
Comment
Send
Share












