፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 17 2016| NBC ETHIOPIA-በደቡብ ኢትዮጵያ ክልል ጎፋ ዞን፣ ገዜ ጎፋ ወረዳ፣ ኬንቾ ሳቻ ጎዝዲ ቀበሌ በተከሰተው የመሬት ናዳ ለተጎዱ ወገኖችና ቤተሰቦቻቸው መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረገ እንደሚገኝ የክልሉ የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች ቢሮ ኃላፊ ወ/ሮ ሰናይት ሰለሞን ገለጹ፡፡
የክልሉ መንግስት አመራርና ባለሙያዎችን ያካተተ ኮሚቴ በማቋቋም ችግሩ በልዩ ትኩረት እየሰራ መሆኑን ገልጸው የፌዴራልና የክልሉ ስራ አመራር ኮሚሽን፣ የኢትዮጵያ ቀይ መስቀል ማህበር እና ሌሎችም አስፈላጊውን ድጋፍ እያደረጉ መሆኑን ተናግረዋል።
እስከ አሁን በተከናወነው ስራ ጉዳት ለደረሰባቸው ወገኖች ሰብዊ ድጋፍ ማድረግን ጨምሮ በሕይወት የተረፉ የህክምና እርዳታ እንዲያገኙና ለጉዳት ተጋላጭ በሆኑ አካባቢዎች የሚኖሩ ሰዎችን የማዘዋወር ተግባር መከናወኑን አስረድተዋል።
የክልሉ መንግስት እያደረገ ካለው ድጋፍ በተጨማሪ ህብረተሰቡ፣ አጎራባች ዞኖችን ጨምሮ አጋር የልማት ድርጅቶች እያደረጉት ያለው ሰብአዊ ድጋፍ ተጠናክሮ መቀጠል እንደሚገባም የቢሮ ኃላፊዋ መግለጻቸውን ኢዜአ ዘግቧል ፡፡
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












