፨ ፨ ፨ ፨ ፨ ፨
አዲስ አበባ | ሐምሌ 16 2016| NBC ETHIOPIA-የሪፐብሊካን ፓርቲ አካላት የሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ስልጣናቸውን ይለቁ ዘንድ አበክረው እየጠየቁ መሆኑ ተሰምቷል፡፡
የአሜሪካው ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ከ2024 የፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ፉክክር መውጣታቸውን ተከትሎ የሪፐብሊካን ፓርቲው አካላት የሀገሪቱን የህዝብ ተወካዮች ምክርቤት አፈጉባኤ ማይክ ጆንሰንን ጨምሮ ባይደን ጊዜ ሳይወስዱ ስልጣናቸውን ይለቁ ዘንድ ብርቱ ጥያቄ ማቅረባቸውን ነው የተሰማው፡፡
የሪፐብሊካን ፓርቲ አካላት በባይደን ላይ ያስነሳቸው ዋናው ነገር ደግሞ ሀገሪቱን ለመምራት ብቃት የላቸውም የሚል ነው፡፡ ባይደን በቡላቸው የተሰጣቸውን የስልጣን ዘመን እንደሚያጠናቅቁ ነው ያስታወቁት፡፡
ዘገባው የቲአርቲ ወርልድ ነው፡፡
በ-ትዕግስቱ በቀለ
YouTube – https://www.youtube.com/@NBCEthiopiaSC
TikTok – https://www.tiktok.com/@nbcethiopia
Facebook -https://www.facebook.com/ethiopiannbc
Telegram-https://t.me/nbcethiopiatv












